ترجمة سورة المرسلات

Sadiq and Sani - Amharic translation
ترجمة معاني سورة المرسلات باللغة الأمهرية من كتاب Sadiq and Sani - Amharic translation .


ተከታታይ ኾነው በተላኩት፣

በኀይል መንፈስን ነፋሾች በኾኑትም፣

መበተንን በታኞች በኾኑትም፤ (ነፋሶች)፣

መለየትን ለይዎች በኾኑትም፣

መገሠጫን (ወደ ነቢያት) ጣይዎች በኾኑትም፣

ምክንያትን ለማስወገድ ወይም ለማስፈራራት (ጣይዎች በኾኑት መላእክት) እምላለሁ፡፡

ያ የምትስፈራሩበት (ትንሣኤ) በእርግጥ ኋኝ ነው፡፡

ከዋክብትም (ብርሃንዋ) በታበሰች ጊዜ፡፡

ሰማይም በተከፈተች ጊዜ፡፡

ጋራዎችም በተንኮተኮቱ ጊዜ፡፡

መልክተኞቹም ወቅት በተደረገላቸው ጊዜ፡፡

ለየትኛው ቀን ተቀጠሩ (የሚባል ሲኾን)፤

ለመለያው ቀን (በተባለ ጊዜ፤ በፍጡሮች መካከል ይፈረዳል)፡፡

የመለያውም ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ?

ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡

የፊተኞቹን (ሕዝቦች) አላጠፋንምን?

ከዚያም የኋለኞቹን እናስከትላቸዋለን፡፡

በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሠራለን፡፡

ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡

ከደካማ ውሃ አልፈጠርናችሁምን?

በተጠበቀ መርጊያ ውስጥም (በማሕፀን) አደረግነው፡፡

እስከ ታወቀ ልክ ድረስ፡፡ መጠንነውም፤ ምን ያማርንም

መጣኞች ነን!

ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡

ምድርን ሰብሳቢ አላደረግናትምን?

ሕያዋን ኾናችሁ ሙታንም ኾናችሁ፡፡

በውስጧም ከፍተኛዎችን ተራራዎች አደረግን፡፡ ጣፋጭ ውሃንም አጠጣናችሁ፡፡

ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡

«ወደዚያ በእርሱ ታስተባብሉ ወደ ነበራችሁት (ቅጣት) አዝግሙ፡፡

«ባለ ሦስት ቅርንጫፎች ወደ ኾነው ጥላ አዝግሙ፤» (ይባላሉ)፡፡

አጠላይ ያልኾነ ከእሳቱም ላንቃ የማያድን ወደ ኾነው (አዝግሙ)፡፡

እርሷ እንደ ታላላቅ ሕንጻ የኾኑን ቃንቄዎች ትወረውራለች፡፡

(ቃንቄውም) ልክ ዳለቻዎች ግመሎችን ይመስላል፡፡

ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡

ይህ የማይናገሩበት ቀን ነው፡፡

ይቅርታም ይጠይቁ ዘንድ፤ ለእነርሱ አይፈቀድላቸውም፡፡

ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡

ይህ መለያው ቀን ነው፡፡ እናንተንም የፊተኞቹንም ሰብሰብናችሁ፡፡

ለናንተም (ለማምለጥ) ብልሃት እንዳላችሁ ተተናኮሉኝ፡፡

ላስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡

ጥንቁቆቹ በጥላዎችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡

ከሚከጅሉትም ሁሉ በፍራፍሬዎች ውስጥ ናቸው፡፡

«ትሠሩት በነበራችሁት ዋጋ የምትደሰቱ ኾናችሁ ብሉ፣ ጠጡም፤» (ይባላሉ)፡፡

እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡

ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡

ብሉ፤ ጥቂትንም (ጊዜ) ተጠቀሙ፡፡ እናንተ አመጸኞች ናችሁና፡፡

ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡

«ለእነርሱ ስገዱም» በተባሉ ጊዜ አይሰግዱም፡፡

ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡

ከእርሱም ሌላ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?
Icon