ترجمة معاني سورة الشورى باللغة الأمهرية من كتاب Sadiq and Sani - Amharic translation
ﰡ
آية رقم 1
ﭑ
ﭒ
ሐ.መ (ሐ፡ ሚም)፡፡
آية رقم 2
ﭓ
ﭔ
ዐ.ሰ.ቀ (ዓይን ሲን ቃፍ)፤
آية رقم 3
እንደዚሁ (በዚህች ሱራ ውስጥ እንዳለው) አሸናፊው ጥበበኛው አላህ ወዳንተ ያወርዳል፡፡ ወደእነዚያም ከአንተ በፊት ወደ ነበሩት ሕዝቦች (አውርዷል)፡፡
آية رقم 4
በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ እርሱም የበላዩ ታላቁ ነው፡፡
آية رقم 5
(ከአላህ ፍራቻ) ሰማያት ከበላያቸው ሊቀደዱ ይቀርባሉ፡፡ መላእክትም ጌታቸውን እያመሰገኑ ያወድሳሉ፡፡ በምድርም ላለው ፍጡር ምሕረትን ይለምናሉ፡፡ ንቁ! አላህ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነው፡፡
آية رقم 6
እነዚያም ከእርሱ ሌላ (የጣዖታት) ረዳቶችን የያዙ፤ አላህ በእነርሱ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ አንተም በእነርሱ ላይ ኀላፊ አይደለህም፡፡
آية رقم 7
እንደዚሁም የከተሞች እናት የኾነችውን (የመካን ሰዎች) በአካባቢዋ ያሉትንም ልታስፈራራ የመሰብሰቢያውንም ቀን በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲኾን ልታስጠነቅቅ ዐረብኛ የኾነን ቁርኣን ወደ አንተ አወረድን፡፡ (ከእነርሱም) ከፊሉ በገነት ውሰጥ ከፊሉም በእሳት ውስጥ ነው፡፡
آية رقم 8
አላህም በሻ ኖሮ (ባንድ ሃይማኖት ላይ) አንድ ሕዝብ ባደረጋቸው ነበር፡፡ ግን የሚሻውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባል፡፡ በዳዮችም ለእነርሱ ወዳጅና ረዳት ምንም የላቸውም፡፡
آية رقم 9
ከእርሱ ሌላ ረዳቶችን ያዙን? (ረዳቶች አይደሉም)፡፡ አላህም ረዳት እርሱ ብቻ ነው፡፡ እርሱም ሙታንን ሕያው ያደርጋል፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡
آية رقم 10
ከምንም ነገር ያ በእርሱ የተለያዩበት ፍርዱ ወደ አላህ ነው፡፡ «እርሱ አላህ ጌታዬ ነው፡፡ በእርሱ ላይ ተጠጋሁ፣ ወደርሱም እመለሳለሁ» (በላቸው)፡፡
آية رقم 11
ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ነው፡፡ ከነፍሶቻችሁ ሴቶችን ከቤት እንስሳዎችም ዓይነቶችን (ወንዶችና ሴቶችን) ለእናንተ አደረገላችሁ፡፡ በእርሱ ያበዛችኋል፡፡ የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡
آية رقم 12
የሰማያትና የምድር (ድልቦች) መከፈቻዎች የእርሱ ናቸው፡፡ ሲሳይን ለሚሻው ሰው ያሰፋል፤ ያጠባልም፡፡ እርሱ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡
آية رقم 13
ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፡፡ ያንንም ወዳንተ ያወረድነውን ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን ሙሳንና ዒሳንም ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም አትለያዩ ማለትን (ደነገግን)፡፡ በአጋሪዎቹ ላይ ያ ወደርሱ የምትጠራቸው ነገር ከበዳቸው፡፡ አላህ የሚሻውን ሰው ወደእርሱ (እምነት) ይመርጣል፡፡ የሚመለስንም ሰው ወደርሱ ይመራል፡፡
آية رقم 14
(የሃይማኖት ሰዎች) ዕውቀቱም ከመጣላቸው በኋላ በመካከላቸው ለምቀኝነት እንጅ ለሌላ አልተለያዩም፡፡ እስከ ተወሰነም ጊዜ (በማቆየት) ከጌታህ ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በእነርሱ መካከል (አሁን) በተፈረደ ነበር፡፡ እነዚያም ከኋላቸው መጽሐፉን እንዲወርሱ የተደረጉት ከእርሱ በእርግጥ በአወላዋይ ጥርጣሬ ውስጥ ናቸው፡፡
آية رقم 15
ለዚህም (ድንጋጌ ሰዎችን) ጥራ፡፡ እንደታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡ ዝንባሌዎቻቸውንም አትከተል፡፡ «በላቸውም ከመጽሐፍ አላህ ባወረደው ሁሉ አመንኩ፡፡ በመካከላችሁም ላስተካክል ታዘዝኩ፡፡ አላህ ጌታችን ጌታችሁም ነው፡፡ ለእኛ ሥራዎቻችን አልሉን፡፡ ለእናንተም ሥራዎቻችሁ አልሏችሁ፡፡ በእኛና በእናንተ መካከል ክርክር የለም፡፡ አላህ በመካከላችን ይሰበስባል፡፡ መመለሻም ወደእርሱ ብቻ ነው፡፡»
آية رقم 16
እነዚያም በአላህ (ሃይማኖት) ለእርሱ ተቀባይ ካገኘ በኋላ የሚከራከሩት ማስረጃቸው በጌታቸው ዘንድ ብልሹ ናት፡፡ በእነርሱም ላይ ቁጣ አልለባቸው፡፡ ለእነርሱም ብርቱ ቅጣት አልላቸው፡፡
آية رقم 17
አላህ ያ መጽሐፉን በእውነት ያወረደ ነው፡፡ ሚዛንንም (እንደዚሁ)፡፡ ሰዓቲቱ ምንአልባት ቅርብ መኾንዋን ምን ያሳውቅሃል?
آية رقم 18
እነዚያ በእርሷ የማያምኑት በእርሷ ያቻኩላሉ፡፡ እነዚያም ያመኑት ከእርሷ ፈሪዎች ናቸው፡፡ እርሷም እውነት መኾንዋን ያውቃሉ፡፡ ንቁ! እነዚያ በሰዓቲቱ የሚከራከሩት በእርግጥ (ከእውነት) በራቀ ስሕተት ውስጥ ናቸው፡፡
آية رقم 19
አላህ በባሮቹ ሩህሩህ ነው፡፡ ለሚሻው ሰው (በሰፊው) ሲሳይን ይሰጣል፡፡ እርሱም ብርቱው አሸናፊው ነው፡፡
آية رقم 20
(በሥራው) የኋለኛይቱን ዓለም አዝመራ የሚፈልግ የኾነ ሰው ለእርሱ በአዝመራው ላይ እንጨምርለታለን፡፡ የቅርቢቱንም ዓለም አዝመራ የሚፈልግ የኾነ ሰው ከእርሷ (የተወሰነለትን ብቻ) እንሰጠዋለን፡፡ ለእርሱም በኋለኛይቱ ዓለም ምንም ፋንታ የለውም፡፡
آية رقم 21
ከሃይማኖት አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነርሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አልሏቸውን? የፍርዱ ቃል ባልነበረ ኖሮ በመካከላቸው (አሁን) በተፈረደ ነበር፡፡ በደለኞችም ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ አልላቸው፡፡
آية رقم 22
በደለኞችን ከሠሩት ሥራ (ዋጋ በትንሣኤ ቀን) ፈሪዎች ኾነው ታያቸዋለህ፡፡ እርሱም በእነርሱ ላይ ወዳቂ ነው፡፡ እነዚያም ያመኑት መልካሞችንም የሠሩት በገነቶች ጨፌዎች ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ የሚሹት ሁሉ አልላቸው፡፡ ይህ እርሱ ታላቅ ችሮታ ነው፡፡
آية رقم 23
ይህ (ታላቅ ችሮታ) ያ አላህ እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ባሮቹን የሚያበስርበት ነው፡፡ «በእርሱ (መልክቴን በማድረሴ) ላይ በዝምድና ውዴታን እንጅ ዋጋን አልጠይቃችሁም» በላቸው፡፡ መልካሚቱንም ሥራ የሚሠራ ሰው ለእርሱ በእርሷ መልካምን ነገር እንጨምርለታለን፡፡ አላህ መሓሪ አመስጋኝ ነውና፡፡
آية رقم 24
ይልቁንም «በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፈ» ይላሉን? አላህም ቢሻ በልብህ ላይ ያትማል፡፡ አላህም ውሸቱን ያብብሳል፡፡ እውነቱንም በቃላቱ ያረጋግጣል፡፡ እርሱ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡
آية رقم 25
እርሱም ያ ከባሮቹ ንስሓን የሚቀበል፣ ከኃጢአቶችም ይቅር የሚል፣ የምትሠሩትንም ሁሉ የሚያውቅ ነው፡፡
آية رقم 26
እነዚያንም ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ልመናቸውን ይቀበላል፡፡ ከችሮታውም ይጨምርላቸዋል፡፡ ከሓዲዎቹም ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አልላቸው፡፡
آية رقم 27
አላህም ለባሮቹ (ሁሉ) ሲሳይን በዘረጋ ኖሮ በምድር ውስጥ (ሁሉም) ወሰን ባለፉ ነበር፡፡ ግን የሚሻውን በልክ ያወርዳል፡፡ እርሱ በባሮቹ ውስጥ ዐዋቂ ተመልካች ነውና፡፡
آية رقم 28
እርሱም ያ ተስፋ ከቆረጡ በኋላ ዝናምን የሚያወርድ ችሮታውንም የሚዘረጋ ነው፡፡ እርሱም ረዳቱ ምስጉኑ ነው፡፡
آية رقم 29
ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ ከተንቀሳቃሽም በሁለቱ ውስጥ የበተነውን (መፍጠሩ) ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ እርሱም በሚሻ ጊዜ እነርሱን በመሰብሰብ ላይ ቻይ ነው፡፡
آية رقم 30
ከመከራም ማንኛውም ያገኛችሁ ነገር እጆቻችሁ በሠሩት (ኃጢኣት) ምክንያት ነው፡፡ ከብዙውም ይቅር ይላል፡፡
آية رقم 31
እናንተም በምድር ውስጥ የምታቅቱ አይደላችሁም፡፡ ለእናንተም ከአላህ ሌላ ከዘመድም ከረዳትም ምንም የላችሁም፡፡
آية رقم 32
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖ
ﭗ
በባሕር ላይ እንደ ጋራዎች ኾነው ተንሻላዮቹም (መርከቦች) ከአስደናቂ ምልክቶቹ ናቸው፡፡
آية رقم 33
ቢሻ ነፋሱን የረጋ ያደርገዋል፡፡ በባሕሩም ጀርባ ላይ ረጊዎች ይኾናሉ፡፡ በዚህ ውሰጥ በጣም ታጋሽና አመስጋኝ ለኾነ ሁሉ በእርግጥ ምልክቶች አልሉ፡፡
آية رقم 34
ወይም በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት (በማስጠም) ያጠፋቸዋል፡፡ ከብዙም ይቅርታ ያደርጋል፡፡
آية رقم 35
(ከእነርሱ ለመበቀል)፤ እነዚያንም በአንቀጾቻችን የሚከራከሩትን ለማወቅ (ያጠፋቸዋል)፡፡ ለእነርሱ ምንም መሸሻ የላቸውም፡፡
آية رقم 36
ከምንም ነገር የተሰጣችሁት የቅርቢቱ ሕይወት መጠቀሚያ ነው፡፡ አላህ ዘንድ ያለውም ምንዳ ለእነዚያ ለአመኑትና በጌታቸው ላይ ለሚጠጉት በላጭና ሁል ጊዜ ነዋሪ ነው፡፡
آية رقم 37
ለእነዚያም የኀጢኣትን ታላላቆችና ጠያፎችን የሚርቁ በተቆጡም ጊዜ እነሱ የሚምሩት ለኾኑት፡፡
آية رقم 38
ለእነዚያም የጌታቸውን ጥሪ ለተቀበሉት፣ ሶላትንም ላዘወተሩት፣ ነገራቸውም በመካከላቸው መመካከር ለኾነው ከሰጠናቸውም ሲሳይ ለሚለግሱት፡፡
آية رقم 39
ﮥﮦﮧﮨﮩﮪ
ﮫ
ለእነዚያም በደል በደረሰባቸው ጊዜ እነርሱ (በመሰሉ) የሚመልሱ ለኾኑት (በላጭና ኗሪ ነው)፡፡
آية رقم 40
የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡ ይቅርም ያለና ያሳመረ ሰው ምንዳው በአላህ ላይ ነው፡፡ እርሱ በደለኞችን አይወድም፡፡
آية رقم 41
ከተበደሉም በኋላ (በመሰሉ) የተበቀሉ እነዚያ በነርሱ ላይ ምንም (የወቀሳ) መንገድ የለባቸውም፡፡
آية رقم 42
(የወቀሳ) መንገዱ በእነዚያ ሰዎችን በሚበድሉት፣ በምድርም ውስጥ ያለ ሕግ ወሰን በሚያልፉት፣ ላይ ብቻ ነው፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አልላቸው፡፡
آية رقم 43
የታገስና ምሕረት ያደረገም ሰው ይህ ከምርሮቹ (ከተፈላጊዎቹ) ነገሮች ነው፡፡
آية رقم 44
አላህ የሚያጠመውም ሰው ከእርሱ በኋለ ለእርሱ ምንም ረዳት የለውም፡፡ በደለኞችንም ቅጣቱን ባዩ ጊዜ ወደ መመለስ መንገድ አልለን? የሚሉ ሲኾኑ ታያቸዋለህ፡፡
آية رقم 45
ከውርደት የተነሳ ፈሪዎች ኾነው በዓይን ስርቆት ወደእርሷ (ወደ እሳት) እያስተዋሉ በእርሷ ላይ የሚቀረቡ ሲኾኑ ታያቸዋለህ፡፡ እነዚያም ያመኑት፡- «በእርግጥ ከሳሪዎቹ እነዚያ ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን በትንሣኤ ቀን ያከሰሩት ናቸው» ይላሉ፡፡
آية رقم 46
ንቁ! በደለኞች በእርግጥ በዘውታሪ ስቃይ ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱም ከአላህ ሌላ የሚረዷቸው ዘመዶች ምንም አልነበሩዋቸውም፡፡ አላህም የሚያጠመው ሰው ለእርሱ (ወደ እውነት) ምንም መንገድ የለውም፡፡
آية رقم 47
ለእርሱ መመለስ የሌለው ቀን ከአላህ ከመምጣቱ በፊት ለጌታችሁ ታዘዙ፡፡ በዚያ ቀን ለእናንተ ምንም መጠጊያ የላችሁም፡፡ ለእናንተም ምንም መካድ የላችሁም፡፡
آية رقم 48
ቢዞሩም (ወቀሳ የለብህም)፡፡ በእነርሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አልላክንህምና፡፡ ባንተ ላይ ማድረስ እንጅ ሌላ የለብህም፡፡ እኛም ሰውን ከእኛ የኾነን ጸጋ ባቀመስነው ጊዜ በርሷ ይደሰታል፡፡ እጆቻቸው ባስቀደሙትም ኀጢአት ምክንያት መከራ ብትደርስባቸው (ተስፋ ይቆርጣሉ)፡፡ ሰው (ውለታን) በጣም ከሐዲ ነውና፡፡
آية رقم 49
የሰማያትና የምድር ንግሥና የአላህ ነው፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ ለሚሻው ሰው ሴቶችን (ልጆች) ይሰጣል፡፡ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል፡፡
آية رقم 50
ወይም ወንዶችና ሴቶች አድርጎ ያጠናዳቸዋል፡፡ የሚሻውንም ሰው መካን ያደርገዋል፡፡ እርሱ ዐዋቂ ቻይ ነውና፡፡
آية رقم 51
ለሰውም አላህ በራእይ፣ ወይም ከግርዶ ወዲያ፣ ወይም መልክተኛን (መልአክን) የሚልክና በፈቃዱ የሚሻውን ነገር የሚያወርድለት ቢኾን እንጅ (በገሃድ) ሊያናግረው ተገቢው አይደለም፡፡ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና፡፡
آية رقم 52
እንደዚሁም ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲኾን መንፈስን (ቁርኣንን) አወረድን፡፡ መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም፡፡ ግን (መንፈሱን) ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው፡፡ አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ፡፡
آية رقم 53
ወደዚያ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ወደ ኾነው አላህ መንገድ (ትመራለህ)፡፡ ንቁ! ነገሮቹ ሁሉ ወደ አላህ ይመለሳሉ፡፡
تقدم القراءة