የሱራ يونس ትርጉም በالأمهرية ከSadiq and Sani - Amharic translation
Verse 1
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖ
ﭗ
አ.ለ.ረ (አሊፍ ላም ራ) ይህቺ (ሱራ) ጥበብ ከተመላው መጽሐፍ (ከቁርኣን) አንቀጾች ናት፡፡
Verse 2
«ሰዎችን አስፈራራ፡፡ እነዚያንም ያመኑትን ለእነሱ ከጌታቸው ዘንድ መልካም ምንዳ ያላቸው መኾኑን አብስር» በማለት ከነርሱው ወደ ኾነ አንድ ሰው ራእይን ማውረዳችን ለሰዎች ድንቅ ኾነባቸውን ከሓዲዎቹ፡- «ይህ በእርግጥ ግልጽ ድግምተኛ ነው» አሉ፡፡
Verse 3
ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፡፡ ከዚያም ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብር ሲኾን በዐርሹ ላይ (ስልጣኑ) ተደላደለ፡፡ ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፡፡ እነሆ! አላህ ጌታችሁ ነውና ተገዙት፤ አትገሰጹምን
Verse 4
ሁላችሁም ኾናችሁ መመለሻችሁ ወደ እርሱ ነው፡፡ (ይህም) የተረጋገጠ የአላህ ቃል ኪዳን ነው፤ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፡፡ ከዚያም እነዚያን ያመኑትንና መልካም የሠሩትን በትክክል ይመነዳ ዘንድ ይመልሰዋል፡፡ እነዚያ የካዱትም ይክዱት በነበሩት ነገር ለነርሱ ከፈላ ውሃ የኾነ መጠጥና አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡
Verse 5
እርሱ ያ ፀሐይን አንጻባራቂ ጨረቃንም አብሪ ያደረገ ነው፡፡ የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን ታውቁ ዘንድም ለእርሱ መስፈሪያዎችን የለካ ነው፡፡ አላህ ይህንን በእውነት እንጂ (በከንቱ) አልፈጠረውም፡፡ ለሚያውቁ ሕዝቦች አንቀጾችን ያብራራል፡፡
Verse 6
ሌሊትና ቀን በመተካካታቸው አላህም በሰማያትና በምድር ውስጥ በፈጠረው ሁሉ ለሚጠነቀቁ ሕዝቦች ምልክቶች አሉ፡፡
Verse 7
እነዚያ መገናኘታችንን የማይፈሩ ቅርቢቱንም ሕይወት የወደዱ በእሷም የረኩ እነዚያም እነሱ ከአንቀጾቻችን ዘንጊዎች የኾኑ፡፡
Verse 8
ﭡﭢﭣﭤﭥﭦ
ﭧ
እነዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት መኖሪያቸው በእሳት ውስጥ ነው፡፡
Verse 9
እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ጌታቸው በእምነታቸው ምክንያት (የገነትን መንገድ) ይመራቸዋል፡፡ ከሥራቸው ወንዞች ይፈስሳሉ፡፡ በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ይኖራሉ፡፡
Verse 10
በእርሷም ውስጥ ጸሎታቸው ጌታችን ሆይ! ጥራት ይገባህ (ማለት) ነው፡፡ በእርሷ ውስጥ መከባበሪያቸውም ሰላም መባባል ነው፤ የመጨረሻ ጸሎታቸውም ምስጋና ለዓለማት ጌታ ይሁን (ማለት) ነው፡፡
Verse 11
አላህ ለሰዎች ደግን ነገር ለማግኘት እንደ መቻኮላቸው (አጥፋን ሲሉት) ክፉን ነገር ቢያስቸኩል ኖሮ ጊዜያቸው ወደነሱ በተፈጸመ ነበር፡፡ እነዚያንም መገናኘታችንን የማይፈሩትን በጥመታቸው ውስጥ የሚዋልሉ ሲኾኑ እንተዋቸዋለን፡፡
Verse 12
ሰውንም ጉዳት ባገኘው ጊዜ በጎኑ ላይ ተጋድሞ ወይም ተቀምጦ ወይም ቆሞ ይለምነናል፡፡ ጉዳቱንም ከእሱ ላይ በገለጥንለት ጊዜ ወደ አገኘው ጉዳት እንዳልጠራን ሆኖ ያልፋል፡፡ እንደዚሁ ለድንበር አላፊዎች ይሠሩት የነበሩት ሥራ ተሸለመላቸው፡፡
Verse 13
ከእናንተ በፊት የነበሩትንም የክፍለ ዘመናት ሰዎች መልክተኞቻቸው በማስረጃዎች የመጧቸው ሲኾኑ በበደሉና የማያምኑም በኾኑ ጊዜ በእርግጥ አጠፋናቸው፡፡ እንደዚሁ ተንኮለኞችን ሕዝቦች እንቀጣለን፡፡
Verse 14
ከዚያም እንዴት እንደምትሠሩ ልንመለከት ከእነሱ በኋላ በምድር ላይ ምትኮች አደረግናችሁ፡፡
Verse 15
አንቀጾቻችንም ግልጽ ኾነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ እነዚያ መገናኘታችንን የማይፈሩት ከዚህ ሌላ የሆነን ቁርኣን አምጣልን ወይም ለውጠው ይላሉ፡፡ እኔ ከራሴ በኩል ልለውጠው አይገባኝም፡፡ ወደእኔ የሚወርደውን እንጂ አልከተልም፡፡ እኔ ከጌታዬ ባምጽ የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራለሁ በላቸው፡፡
Verse 16
አላህ በሻ ኖሮ በእናንተ ላይ ባለነበብኩትም (አላህ) እርሱን ባላሳወቃችሁም ነበር፡፡ በእናንተም ውስጥ ከእርሱ በፊት (ምንም ሳልል) ብዙን ዕድሜ በእርግጥ ኖሬአለሁ፤ አታውቁምን
Verse 17
በአላህም ላይ እብለትን ከቀጣጠፈ ወይም በአንቀጾቹ ከአስተባበለ ይበልጥ በዳይ ማን ነው እነሆ አመጸኞች አይድኑም፡፡
Verse 18
ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ይግገዛሉ፡፡ «እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው» ይላሉ፡፡ «አላህን በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን» በላቸው፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፤ ላቀም፡፡
Verse 19
ሰዎችም አንድ ሕዝብ እንጂ ሌላ አልነበሩም፡፡ ተለያዩም፡፡ ከጌታህ ያለፈች ቃልም ባልነበረች ኖሮ በእርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው በእርግጥ (በቶሎ) በተፈረደ ነበር፡፡
Verse 20
በእርሱ ላይም ከጌታው የሆነች ተዓምር ለምን አትወረድለትም ይላሉ፡፡ «ሩቅ ነገርም ሁሉ የአላህ ብቻ ነው፡፡ ተጠባበቁም፤ እኔ ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝና» በላቸው፡፡
Verse 21
ሰዎችንም ካገኛቸው ጉዳት በኋላ እዝነትን (ዝናብና ምቾትን) ባቀመስናቸው ጊዜ ወዲያውኑ ለእነሱ በተዓምራቶቻችን (በማላገጥ) ተንኮል ይኖራቸዋል፡፡ አላህ ቅጣተ ፈጣን ነው፡፡ «መልክተኞቻችን የምትመክሩትን ነገር በእርግጥ ይጽፋሉ» በላቸው፡፡
Verse 22
እርሱ (አላህ) ያ በየብስና በባሕር የሚያስኬዳችሁ ነው፡፡ በመርከቦችም ውስጥ በሆናችሁና በእነርሱም በመልካም ነፋስ በርሷ የተደሰቱ ኾነው (መርከቦቹ) በተንሻለሉ ጊዜ ኀይለኛ ነፋስ ትመጣባታለች፡፡ ከየስፍራውም ማዕበል ይመጣባቸዋል፡፡ እነሱም (ለጥፋት) የተከበቡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ (ያን ጊዜ) አላህን ከዚህች (ጭንቀት) ብታድነን በእርግጥ ከአመስጋኞቹ እንሆናለን ሲሉ ሃይማኖትን ለርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው ይለምኑታል፡፡
Verse 23
በአዳናቸውም ጊዜ እነሱ ወዲያውኑ ያለ አግባብ በምድር ላይ ወሰን ያልፋሉ፡፡ እናንተ ሰዎች ሆይ! ወሰን ማለፋችሁ (ጥፋቱ) በነፍሶቻችሁ ላይ ብቻ ነው፡፡ (እርሱም) የቅርቢቱ ሕይወት መጠቀሚያ ነው፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደኛ ነው፡፡ ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እንነግራችኋለን፡፡
የቅርቢቱ ሕይወት ምሳሌ ከሰማይ እንዳወረድነው ውሃ፣ በእርሱም ሰውና እንስሳዎች ከሚበሉት የምድር በቃይ ተቀላቅሎበት (እንደ ፋፋ) ምድርም ውበትዋን በያዘችና ባጌጠች ጊዜ ባለቤቶችዋም በርሷ ላይ እነርሱ ቻዮች መኾናቸውን ባሰቡ ጊዜ ትእዛዛችን ሌሊት ወይም ቀን መጥቶባት ትላንት እንዳልነበረች የታጨደች እንዳደረግናት ብጤ ነው፡፡ እንደዚሁም ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች አንቀጾችን እናብራራለን፡፡
Verse 25
አላህም ወደ ሰላም አገር ይጠራል፡፡ የሚሻውንም ሰው ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል፡፡
Verse 26
ለእነዚያ መልካም ለሠሩት መልካም ነገርና ጭማሪም አላቸው፡፡ ፊቶቻቸውንም ጥቁረትና ውርደት አይሸፍናቸውም፡፡ እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡
Verse 27
ለእነዚያም ኃጢአቶችን ለሠሩት የኃጢኣቲቱ ቅጣት በብጤዋ አለቻቸው፡፡ ውርደትም ትሸፍናቸዋለች፡፡ ለእነሱ ከአላህ (ቅጣት) ጠባቂ የላቸውም፡፡ ፊቶቻቸው ከጨለመ ሌሊት ቁራጮች እንደ ተሸፈኑ ይኾናሉ፡፡ እነዚያ የእሳት ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘለዓለም ነዋሪዎች ናቸው፡፡
Verse 28
ሁሉንም የምንሰበስባቸውን ከዚያም ለእነዚያ ለአጋሩት እናንተም ተጋሪዎችሁም ስፍራችሁን ያዙ የምንልበትን ተጋሪዎቻቸውም እኛን ትገዙ አልነበራችሁም የሚሉዋቸው ሲኾኑ በመካከላቸው የምንለይበትን ቀን (አስታውስ)፡፡
Verse 29
«(ጣዖታቶቹ ለእኛ) ከመገዛታችሁ በእርግጥ ዘንጊዎች ለመኾናችንም በእኛና በእናንተ መካከል የአላህ መስካሪነት በቃ» (ይሏቸዋል)፡፡
Verse 30
በዚያ ቀን ነፍስ ሁሉ ያሳለፈችውን ሥራ ታውቃለች፡፡ (አጋሪዎች) ወደ አላህም እውነተኛ ወደ ሆነው ጌታቸው ይመለሳሉ፡፡ ከእነሱም ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር ይጠፋቸዋል፡፡
Verse 31
«ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ ማን ነው ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው» በላቸው፡፡ «በእርግጥም አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ (ለምን ታጋራላችሁ) አትፈሩትምን» በላቸው፡፡
Verse 32
እርሱ እውነተኛ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእውነትም በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ ምን አለ (ከውነት) እንዴት ትዞራላችሁ
Verse 33
እንደዚሁ የጌታህ ቃል በእነዚያ ባመጹት ላይ እነርሱ የማያምኑ መሆናቸው ተረጋገጠች፡፡
Verse 34
«ከምታጋሩዋቸው (ጣዖታት) ውስጥ መፍጠርን የሚጀምር ከዚም የሚመልሰው አለን» በላቸው፡፡ «አላህ መፍጠርን ይጀምራል፤ ከዚያም ይመልሰዋል፡፡ ታዲያ (ከእምነት) እንዴት ትዞራላችሁ» በላቸው፡፡
Verse 35
«ከምታጋሩዋቸው፤ ወደ እውነት የሚመራ አለን» በላቸው፡፡ «አላህ ወደ እውነቱ ይመራል፡፡ ወደ እውነት የሚመራው ሊከተሉት የተገባው ነውን ወይስ ካልተመራ በስተቀር የማይመራው ለእናንተም ምን (አስረጅ) አላችሁ እንዴት (በውሸት) ትፈርዳላችሁ» በላቸው፡፡
Verse 36
አብዛኞቻቸውም ጥርጣሬን እንጂ አይከተሉም፡፡ ጥርጣሬ ከእውነት ምንም አያብቃቃም፡፡ አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
Verse 37
ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ (ከሆነ ፍጡር) የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፡፡ ግን ያንን ከእርሱ በፊት ያለውን (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥና በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ (የተወረደ) ነው፡፡
Verse 38
በእውነትም «(ሙሐመድ) ቀጣጠፈው» ይላሉን «ይህ ከሆነ መሰሉን (አንዲት) ሱራ አምጡ፡፡ ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን ሁሉ (ረዳት) ጥሩ፡፡ እውነተኞች እንደሆናችሁ (ተጋግዛችሁ አምጡ)» በላቸው፡፡
Verse 39
ይልቁንም (ከቁርኣን) እውቀቱን ባላደረሱት ፍቹም ገና ባልመጣቸው ነገር አስተባበሉ፡፡ እንደዚሁ እነዚያ ከእነሱ በፊት የነበሩት አስተባብለዋል፡፡ የበዳዮችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከት፡፡
Verse 40
ከእነርሱም ውስጥ (ወደፊት) በርሱ የሚያምኑ አልሉ፡፡ ከእነርሱም በእርሱ የማያምኑ አልሉ፡፡ ጌታህም አጥፊዎቹን በጣም ዐዋቂ ነው፡፡
Verse 41
«ቢያስተባብሉህም ለእኔ ሥራዬ አለኝ፡፡ ለእናንተም ሠራችሁ አላችሁ፡፡ እናንተ ከምሠራው ነገር ንጹሕ ናችሁ፡፡ እኔም ከምትሠሩት ነገር ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡
Verse 42
ከእነሱም ወደ አንተ የሚያዳምጡ (እና የማያምኑ) አልሉ፡፡ አንተ ደንቆሮዎችን የማያውቁ ቢኾኑም ታሰማለህን
Verse 43
ከእነሱም ወደ አንተ የሚመለከቱ አልሉ፡፡ አንተ (ልበ) ዕውራንን የማያዩ ቢኾኑም ትመራለህን
Verse 44
አላህ ሰዎችን ምንም አይበድልም፡፡ ግን ሰዎች ነፍሶቻቸውን ይበድላሉ፡፡
Verse 45
(ከሓዲዎችን) ከቀን አንዲትን ሰዓት እንጂ እንዳልቆዩ መስለው በመካከላቸው የሚተዋወቁ ሲሆኑ በምንሰበስባቸው ቀን (አስታውስ)፡፡ እነዚያ በአላህ መገናኘት ያስተባበሉት በእርግጥ ከሰሩ የተመሩም አልነበሩም፡፡
Verse 46
የዚያንም የምናስፈራራቸውን ከፊሉን (በሕይወትህ) ብናሳይህ (መልካም ነው)፡፡ ወይም (ሳናሳይህ) ብንገድልህ መመለሻቸው ወደ እኛ ነው፡፡ ከዚያም አላህ በሚሠሩት ስራ ላይ ዐዋቂ ነው፡፡
Verse 47
ለሕዝቦችም ሁሉ መልክተኛ አላቸው፡፡ መልክተኛውም በመጣ ጊዜ (ሲያስተባብሉ) በመካከላቸው በትክክል ይፈረዳል፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡
Verse 48
«እውነተኞችም ከሆናችሁ ይህ (የቅጣቱ) ቀጠሮ መቼ ነው» ይላሉ፡፡
Verse 49
«ለራሴ ጉዳትንም ጥቅምንም አላህ ከሻው በስተቀር አልችልም፡፡ ለሕዝቦች ሁሉ የተወሰነ ጊዜ አልላቸው፡፡ ጊዜያቸው በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይቆዩም፤ አይቀደሙምም» በላቸው፡፡
Verse 50
«ቅጣቱ በሌሊት ወይም በቀን ቢመጣባችሁ፤ አጋሪዎቹ ከርሱ የሚቻኮሉበት ነገር ምንድን ነው ንገሩኝ» በላቸው፡፡
Verse 51
«ከዚያም (ቅጣቱ) በወደቀ ጊዜ በእርሱ አመናችሁበትን በእርግጥ በእርሱ የምትቻኮሉ የነበራችሁ ስትሆኑ አሁን» (ይባላሉ)፡፡
Verse 52
ከዚያም ለእነዚያ ለበደሉት፡- «ዘውታሪን ቅጣት ቅመሱ ትሠሩት የነበረችሁትን ዋጋ እንጂ አትመነዱም» ይባላሉ፡፡
Verse 53
እርሱም «እውነት ነውን» (ሲሉ) ይጠይቁሃል፡፡ «አዎን፤ በጌታዬ እምላለሁ፤ እርሱ እውነት ነው፡፡ እናንተም አምላጮች አይደላችሁም፤» በላቸው፡፡
Verse 54
ለበደለችም ነፍስ ሁሉ በምድር ላይ ያለው ሁሉ ቢኖራት ኖሮ በእርግጥ በተበዠችበት ነበር፡፡ ቅጣቱንም ባዩ ጊዜ ጸጸትን ይገልጻሉ፡፡ በመካከላቸውም በትክክል ይፈረዳል፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡
Verse 55
ንቁ! በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ ንቁ! የአላህ ተስፋ ቃል እርግጥ ነው፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡
Verse 56
ﭻﭼﭽﭾﭿ
ﮀ
እርሱ ሕያው ያደርጋል፤ ይገድላልም ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፡፡
Verse 57
እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሳጼ በደረቶች ውስጥም ላለው (የመጠራጠር በሽታ) መድኃኒት ለምእምናንም ብርሃንና እዝነት በእርግጥ መጣችላችሁ፡፡
Verse 58
«በአላህ ችሮታና በእዝነቱ (ይደሰቱ)፡፡ በዚህም ምክንያት ይደሰቱ፡፡ እርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው» በላቸው፡፡
Verse 59
«አላህ ከሲሳይ ለእናንተ ያወረደውን ከእርሱም እርምና የተፈቀደ ያደረጋችሁትን አያችሁን» በላቸው፡፡ «አላህ (ይህንን) ለእናንተ ፈቀደላችሁን ወይስ በአላህ ላይ ትቀጣጥፋላችሁ» በላቸው፡፡
Verse 60
የእነዚያም በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ (ሰዎች) በትንሣኤ ቀን (በአላህ) ጥርጣሬያቸው ምንድን ነው (አይቀጡም ይመስላቸዋልን) አላህ በሰዎች ላይ (ቅጣትን ባለማቻኮል) የልግስና ባለቤት ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ አያመሰግኑም፡፡
(ሙሐመድ ሆይ!) በማንኛውም ነገር ላይ አትሆንም፣ ከርሱም ከቁርኣን አታነብም፣ ማንኛውንም ሥራ (አንተም ሰዎቹም) አትሠሩም በገባችሁበት ጊዜ በናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ብንሆን እንጂ፡፡ በምድርም ሆነ በሰማይ የብናኝ ክብደት ያክል ከጌታህ (ዕውቀት) አይርቅም፡፡ ከዚያም ያነሰ የተለቀም የለም፤ በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈ ቢሆን እንጂ፡፡
Verse 62
ንቁ! የአላህ ወዳጆች በእነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም፡፡
Verse 63
ﭜﭝﭞﭟ
ﭠ
(እነሱም) እነዚያ ያመኑትና ይፈሩት የነበሩ ናቸው፡፡
Verse 64
ለእነሱ በቅርቢቱ ሕይወትም በመጨረሻይቱም ብስራት አላቸው፤ የአላህ ቃላት መለወጥ የላትም፤ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡
Verse 65
ንግግራቸውም አያሳዝንህ፡፡ ኀይል ሁሉ በሙሉ የአላህ ብቻ ነውና፡፡ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡
Verse 66
ንቁ! በሰማያት ያሉትና በምድርም ያሉት ሁሉ በእርግጥ የአላህ ናቸው፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ ተጋሪዎችን የሚጠሩ ምንን ይከተላሉ ጥርጣሬን እንጂ ሌላ አይከተሉም፡፡ እነርሱም የሚዋሹ እንጂ አይደሉም፡፡
Verse 67
እርሱ ያ ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት (ጨለማ)፤ ቀንንም (ልትሠሩበት) ብርሃን ያደረገላችሁ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ሕዝቦች በእርግጥ ታምራቶች አሉ፡፡
Verse 68
«አላህ ልጅን ያዘ (ወለደ)» አሉ፡፡ (ከሚሉት) ጥራት ተገባው፡፡ እርሱ ተብቃቂ ነው፡፡ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የርሱ ነው፡፡ እናንተ ዘንድ በዚህ (በምትሉት) ምንም አስረጅ የላችሁም፡፡ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን
Verse 69
«እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ ፈጽሞ አይድኑም፤» በላቸው፡፡
Verse 70
(እነሱ) በቅርቢቱ ዓለም መጠቀም አላቸው፡፡ ከዚያም መመለሻቸው ወደእኛ ነው፡፡ ከዚያም ይክዱ በነበሩት ምክንያት ብርቱን ቅጣት እናቀምሳቸዋለን፡፡
Verse 71
የኑሕንም ወሬ በእነሱ ላይ አንብብላቸው፡፡ ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! በእናንተ ውስጥ ብዙ ጊዜ መቆየቴ በአላህም ተዓምራት ማስታወሴ በእናንተ ላይ የከበደ ቢሆን፤ በአላህ ላይ ተጠግቻለሁ፡፡ ነገራችሁንም ከምታጋሩዋቸው (ጣዖታት) ጋር ሆናችሁ ቁረጡ፡፡ ከዚያም ነገራችሁ በእናንተ ላይ ድብቅ አይሁን (ግለጹት)፡፡ ከዚያም (የሻችሁትን) ወደእኔ አድርሱ፡፡ ጊዜም አትስጡኝ (ከምንም አልቆጥራችሁም)፡፡»
Verse 72
«ብትሸሹም (አትጎዱኝም)፡፡ ከምንዳ ምንንም አልለምናችሁምና፡፡ ምንዳዬ በአላህ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም፡፡ ከሙስሊሞች እንድሆንም ታዝዣለሁ፡፡»
Verse 73
አስተባበሉትም፡፡ እርሱንና ከእርሱ ጋር የነበሩትንም በታንኳይቱ ውስጥ አዳንናቸው፡፡ (ለጠፉት) ምትኮችም አደረግናቸው፡፡ እነዚያንም በአንቀጾቻችን ያስተባበሉትን አሰጠምን፡፡ የተስፈራሩትም ሕዝቦች መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት፡፡
Verse 74
ከዚያም ከእርሱ በኋላ መልክተኞችን ወደየሕዝቦቻቸው ላክን፡፡ በግልጽ ማስረጃዎችም መጧቸው፡፡ (ከመላካቸው) በፊት በእርሱ ባስተባበሉበትም ነገር፤ የሚያምኑ አልሆኑም፡፡ እንደዚሁ በወሰን አላፊዎች ልቦች ላይ እናትማለን፡፡
Verse 75
ከዚያም ከእነሱ ኋላ ሙሳንና ሃሩንን ወደ ፈርዖንና ወደ መማክርቱ በተዓምራታችን ላክን፡፡ ኮሩም ትዕቢተኞች ሕዝቦችም ነበሩ፡፡
Verse 76
ከእኛም ዘንድ እውነቱ በመጣላቸው ጊዜ «ይህ በእርግጥ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ፡፡
Verse 77
ሙሳ አለ፡- «እውነቱን በመጣላችሁ ጊዜ ድግምተኞች የማይድኑ ሲኾኑ (እርሱ ድግምት ነው) ትላላችሁን ይህ ድግምት ነውን»
Verse 78
(እነርሱም) አሉ፡- «አባቶቻችንን በእርሱ ላይ ካገኘንበት ሃይማኖት ልታዞረን ለእናንተም በምድር ውስጥ ኩራት (ሹመት) ልትኖራችሁ መጣህብን እኛም ለእናንተ አማኞች አይደለንም፡፡»
Verse 79
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖ
ﭗ
ፈርዖንም፡- «ዐዋቂ ድግምተኛን ሁሉ አምጡልኝ» አለ፡፡
Verse 80
ድግምተኞቹም በመጡ ጊዜ ሙሳ ለእነርሱ፡- «እናንተ የምትጥሉትን ነገር ጣሉ» አላቸው፡፡
Verse 81
(ገመዶቻቸውን) በጣሉም ጊዜ ሙሳ አለ፡- «ያ በርሱ የመጣችሁበት ነገር ድግምት ነው፡፡ አላህ በእርግጥ ያፈርሰዋል፡፡ አላህ የአጥፊዎችን ሥራ ፈጽሞ አያበጅምና፡፡»
Verse 82
አላህም ከሓዲዎች ቢጠሉም እውነትን በቃላቱ ያረጋግጣል፡፡
Verse 83
ለሙሳም ከፈርዖንና ከሹማምንቶቻቸው ማሰቃየትን ከመፍራት ጋር ከወገኖቹ የኾኑ ጥቂቶች ትውልዶች እንጂ አላመኑለትም፡፡ ፈርዖንም በምድር ላይ በእርግጥ የኮራ ነበር፡፡ እርሱም በእርግጥ ወሰን ካለፉት ነበር፡፡
Verse 84
ሙሳም አለ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! በአላህ አምናችሁ እንደ ሆነ በርሱ ላይ ተጠጉ፡፡ ታዛዦች እንደ ሆናችሁ (በአላህ ላይ ትመካላችሁ)፡፡»
Verse 85
አሉም፡- «በአላህ ላይ ተጠጋን፡፡ ጌታችን ሆይ! ለበደለኞች ሕዝቦች መፈተኛ አታድርገን፡፡»
Verse 86
ﮮﮯﮰﮱﯓ
ﯔ
በእዝነትህም ከከሓዲዎች ሕዝቦች አድነን፡፡
Verse 87
ወደ ሙሳና ወደ ወንድሙ፡- «ለሕዝቦቻችሁ በምስር ቤቶችን ሥሩ፡፡ ቤቶቻችሁንም መስገጃ አድርጉ፡፡ ሶላትንም በደንቡ ስገዱ፡፡ (ለሙሳ) ምእምናኖቹንም አብስር» ስንል ላክን፡፡
Verse 88
ሙሳም አለ፡- «ጌታችን ሆይ! አንተ ለፈርዖንና ለሹሞቹ በቅርቢቱ ሕይወት ጌጥን ብዙ ገንዘቦችንም በእርግጥ ሰጠህ፡፡ ጌታችን ሆይ! ከመንገድህ ያሳስቱ ዘንድ (ሰጠሃቸው)፡፡ ጌታችን ሆይ! ገንዘቦቻቸውን አጥፋ፡፡ በልቦቻቸውም ላይ አትም፡፡ አሳማሚን ቅጣት እስከሚያዩ አያምኑምና፡፡»
Verse 89
(አላህም) «ጸሎታችሁ በእርግጥ ተሰምታለች፡፡ ቀጥም በሉ፡፡ የእነዚያንም የማያውቁትን ሰዎች መንገድ አትከተሉ» አላቸው፡፡
Verse 90
የእስራኤልንም ልጆች ባሕሩን አሳለፍናቸው፡፡ ፈርዖንና ሰራዊቱም ወሰን ለማለፍና ለመበደል ተከተሏቸው፡፡ መስጠምም ባገኘው ጊዜ፡- «አመንኩ፡፡ እነሆ ከዚያ የእስራኤል ልጆች በርሱ ከአመኑበት በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ እኔም ከታዛዦቹ ነኝ» አለ፡፡
Verse 91
ከአሁን በፊት በእርግጥ ያመጽክ ከአጥፊዎችም የነበርክ ስትሆን አሁን (አመንኩ ትላለህ)
Verse 92
ዛሬማ ከኋላህ ላሉት ተዓምር ትሆን ዘንድ በድን ሆነህ (ከባሕሩ) እናወጣሃለን (ተባለ)፡፡ ከሰዎችም ብዙዎቹ ከተዓምራታችን በእርግጥ ዘንጊዎች ናቸው፡፡
Verse 93
የእስራኤልንም ልጆች ምስጉንን ስፍራ በእርግጥ አሰፈርናቸው፡፡ ከመልካም ሲሳዮችም ሰጠናቸው፡፡ ዕውቀትም (ቁርኣን) እስከመጣቸው ድረስ አልተለያዩም፡፡ ጌታህ በርሱ ይለያዩበት በነበሩት ነገር በትንሣኤ ቀን በመካከላቸው ይፈርዳል፡፡
Verse 94
ወደ አንተም ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትሆን እነዚያን ከአንተ በፊት መጽሐፉን የሚያነቡትን ጠይቅ፡፡ እውነቱ ከጌታህ ዘንድ በእርግጥ መጥቶልሃል፡፡ ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን፡፡
Verse 95
ከእነዚያም የአላህን አንቀጾች ከአስተባበሉት አትሁን፡፡ ከከሳሪዎቹ ትሆናለህና፡፡
Verse 96
እነዚያ በእነርሱ ላይ የጌታህ ቃል የተረጋገጠባቸው አያምኑም፡፡
Verse 97
ተዓምር ሁሉ ብትመጣላቸውም አሳማሚን ቅጣት እስከሚያዩ ድረስ (አያምኑም)፡፡
Verse 98
(ከዩኑስ በፊት ካለፉት ከተሞች) ያመነችና እምነትዋ የጠቀማት ከተማ ለምን አልኖረችም ግን የዩኑስ ሕዝቦች ባመኑ ጊዜ በቅርቢቱ ሕይወት የውርደትን ቅጣት ከእነሱ ላይ አነሳንላቸው፡፡ እስከ ጊዜም ድረስ አጣቀምናቸው፡፡
Verse 99
ጌታህም በሻ ኖሮ በምድር ያሉት ሰዎች ሁሉም የተሰበሰቡ ሆነው ባመኑ ነበር፡፡ ታዲያ አንተ ሰዎችን አማኞች እንዲኾኑ ታስገድዳለህን
Verse 100
ለማንኛዋም ነፍስ በአላህ ፈቃድ ቢሆን እንጂ ልታምን (ችሎታ) የላትም፡፡ (አላህ ለከፊሎቹ እምነትን ይሻል)፡፡ በእነዚያም በማያውቁት ላይ ርክሰትን ያደርጋል፡፡
Verse 101
«በሰማያትና በምድር ያለውን (ተዓምር) ተመልከቱ» በላቸው፡፡ ተዓምራቶችና አስፈራሪዎችም ለማያምኑ ሕዝቦች አይጠቅሙም፡፡
Verse 102
የእነዚያን ከእነሱ በፊት ያለፉትን ሕዝቦች ቀኖች ብጤ እንጂ ሌላን ይጠባበቃሉን «ተጠባበቁ፤ እኔ ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝ» በላቸው፡፡
Verse 103
ከዚያም መልክተኞቻችንን እነዚያንም ያመኑትን እናድናለን፡፡ እንደዚሁም ምእምናንን (ከጭንቅ ሁሉ) እናድናለን፡፡ (ይህ) በእኛ ላይ ተረጋገጠ፡፡
Verse 104
«እናንተ ሰዎች ሆይ! ከእኔ ሃይማኖት በመጠራጠር ውስጥ ብትሆኑ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን አልገዛም፡፡ ግን ያንን የሚገድላችሁን አላህን እገዛለሁ፡፡ ከምእምናን እንድሆንም ታዝዣለሁ» በላቸው፡፡
Verse 105
ፊትህንም (ወደ ቀጥታ) ያዘነበልክ ስትሆን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ ከአጋሪዎቹም አትሁን፡፡
Verse 106
«ከአላህም በቀር የማይጠቅምንና የማይጎዳን አትገዛ፡፡ ብትሠራም አንተ ያንጊዜ ከበደለኞቹ ትሆናለህ» (ተብያለሁ በላቸው)፡፡
Verse 107
አላህም ጉዳትን ቢያደርስብህ ከእርሱ ሌላ ለእርሱ ገላጭ የለውም፡፡ በጎንም ነገር ቢሻልህ ለችሮታው መላሽ የለም፡፡ ከባሮቹ የሚሻውን በእርሱ ይለይበታል፡፡ እርሱም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
Verse 108
«እናንተ ሰዎች ሆይ! እውነቱ ከጌታችሁ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ (በእርሱ) የተመራም ሰው የሚመራው ለራሱ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው የሚሳሳተው (ጉዳቱ) በራሱ ላይ ነው፡፡ እኔም በእናንተ ላይ ተጠባበቂ አይደለሁም» በላቸው፡፡
Verse 109
ወዳንተም የሚወረደውን ነገር ተከተል፡፡ አላህም (በነሱ ላይ) እስከሚፈርድ ድረስ ታገስ፡፡ እርሱም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነው፡፡
تقدم القراءة