የሱራ العنكبوت ትርጉም በالأمهرية ከSadiq and Sani - Amharic translation
Verse 1
ﮡ
ﮢ
አ.ለ.መ (አሊፍ ላም ሚም)
Verse 2
ሰዎቹ አምነናል በማለታቸው ብቻ እነሱ ሳይፈተኑ የሚተው መኾናቸውን ጠረጠሩን
Verse 3
እነዚያንም ከእነሱ በፊት የነበሩትን በእርግጥ ፈትነናል፡፡ እነዚያንም እውነት የተናገሩትን አላህ በእርግጥ ያውቃል፡፡ ውሸታሞቹንም ያውቃል፡፡
Verse 4
ይልቁንም እነዚያ መጥፎዎችን ሥራዎች የሚሠሩት ሊያመልጡን ይጠረጥራሉን ያ የሚፈርዱት (ፍርድ) ከፋ፡፡
Verse 5
የአላህን መገናኘት ተስፋ የሚያደርግ ሰው (ይዘጋጅ)፡፡ የአላህ ቀጠሮ በእርግጥ መጪ ነውና፡፡ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡
Verse 6
የታገለ ሰውም የሚታገለው ለነፍሱ ነው፡፡ አላህ ከዓለማት በእርግጥ ተብቃቂ ነውና፡፡
Verse 7
እነዚያም ያመኑ፤ መልካሞችንም የሠሩ መጥፎዎቹን ሥራዎቻቸውን ከእነሱ ላይ እናብስላቸዋለን፡፡ በዚያም ይሠሩት በነበሩት መልካም ሥራ በእርግጥ እንመነዳቸዋለን፡፡
Verse 8
ሰውንም በወላጆቹ መልካም አድራጎትን አዘዝነው፡፡ ላንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን (ጣዖት) በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህ አትታዘዛቸው፡፡ መመለሻችሁ ወደኔ ነው፡፡ ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፡፡
Verse 9
እነዚያንም ያመኑ፤ መልካም ሥራዎችንም የሠሩ በደጋጎቹ ውስጥ በእርግጥ እናገባቸዋለን፡፡
Verse 10
ከሰዎችም በአላህ አመንን የሚል ሰው አልለ፡፡ በአላህም (በማመኑ) በተሰቃየ ጊዜ የሰዎችን ማሰቃየት እንደ አላህ ቅጣት ያደርጋል፡፡ ከጌታህም እርዳታ ቢመጣ እኛ በእርግጥ ከእናንተ ጋር ነበርን ይላሉ፡፡ አላህ በዓለማት ሕዝብ ልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ አይደለምን
Verse 11
ﮠﮡﮢﮣﮤﮥ
ﮦ
አላህም እነዚያን ያመኑትን በእርግጥ ያውቃል፡፡ መናፍቆቹንም ያውቃል፡፡
Verse 12
እነዚያም የካዱት ሰዎች ለእነዚያ ላመኑት «መንገዳችንን ተከተሉ፤ ኀጢአቶቻችሁንም እንሸከማለን» አሉ፡፡ እነርሱም ከኀጢአቶቻቸው ምንንም ተሸካሚዎች አይደሉም፡፡ እነርሱ በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡
Verse 13
ሸክሞቻቸውንና ከሸክሞቻቸው ጋር (ሌሎች) ሸክሞችንም በእርግጥ ይሸከማሉ፡፡ በትንሣኤም ቀን ይቀጥፉት ከነበሩት በእርግጥ ይጠየቃሉ፡፡
Verse 14
ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ በውስጣቸውም ሺህ ዓመትን አምሳ ዓመት ሲቀር ተቀመጠ፡፡ እነርሱ በዳዮች ኾነውም የውሃው ማጥለቅለቅ ያዛቸው፡፡
Verse 15
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖ
ﭗ
ኑሕንና የመርከቢቱንም ጓዶች አዳናቸው፡፡ እርሷንም ለዓለማት ተዓምር አደረግናት፡፡
Verse 16
ኢብራሂምንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «አላህን ተገዙ ፍሩትም፡፡ ይህ የምታውቁ ብትሆኑ ለእናንተ በላጭ ነው፡፡
Verse 17
«ከአላህ ሌላ የምትገዝዙት ጣዖታትን ብቻ ነው፡፡ ውሸትንም ትቀጣጥፋላችሁ፡፡ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትግገዙዋቸው ለእናንተ ሲሳይን ሊሰጧችሁ አይችሉም፡፡ ስለዚህ ሲሳይን ከአላህ ዘንድ ብቻ ፈልጉ፡፡ ተገዙትም፡፡ ለእርሱም አመሰግኑ፡፡ ወደእርሱ ትመለሳላችሁ፡፡
Verse 18
«ብታስተባብሉም ከፊታችሁ የነበሩት ሕዝቦች በእርግጥ አስተባብለዋል፡፡ በመልክተኛውም ላይ ግልጽ ማድረስ እንጂ ሌላ የለበትም፡፡»
Verse 19
አላህ መፍጠርን እንዴት እንደሚጀመር ከዚያም እንዴት እንደሚመልሰው አይመለከቱምን ይህ በአላህ ላይ ቀላል ነው፡፡
Verse 20
«፡--በምድር ላይ ኺዱ፤ መፍጠርንም እንዴት እንደ ጀመረ ተመልከቱ፡፡ ከዚያም፤ አላህ የመጨረሻይቱን መነሳት ያስነሳል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና» በላቸው፡፡
Verse 21
የሚሻውን ሰው ይቀጣል፡፡ የሚሻውንም ሰው ያዝንለታል፡፡ ወደእርሱም ትመለሳላችሁ፡፡
Verse 22
እናንተም በምድርም ኾነ በሰማይ የምታቅቱ አይደላችሁም፡፡ ከአላህም ሌላ ረዳትም ተከላካይም ምንም የላችሁም፡፡
Verse 23
እነዚያም በአላህ አንቀጾችና በመገናኘቱ የካዱ እነዚያ ከእዝነቴ ተስፋን ቆረጡ፡፡ እነዚያም ለእነሱ አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡
Verse 24
የሕዝቦቹም መልስ፡- «ግደሉት፤ ወይም አቃጥሉት» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡ ከእሳቲቱም አላህ አዳነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች ተዓምራቶች አሉበት፡፡
Verse 25
(ኢብራሂም) አለም «ከአላህ ሌላ ጣዖታትን (አማልክት) የያዛችሁት በቅርቢቱ ሕይወት በመካከላችሁ ለመዋደድ ብቻ ነው፡፡ ከዚያም በትንሣኤ ቀን ከፊላቸሁ በከፊሉ ይክዳል፡፡ ከፊላችሁም ከፊሉን ይረግማል፡፡ መኖሪያችሁም እሳት ናት፡፡ ለእናንተም ከረዳቶች ምንም የላችሁም፡፡»
Verse 26
ሉጥም ለእርሱ አመነ፤ (ኢብራሂም) «እኔ ወደ ጌታዬ ተሰዳጅ ነኝ፡፡ እነሆ እርሱ አሸናፊው ጥበበኛው ነውና» አለም፡፡
Verse 27
ለእርሱም ኢስሐቅንና ያዕቆብን ሰጠነው፡፡ በዘሩም ውስጥ ነብይነትንና መጽሐፍን አደረግን፡፡ ምንዳውንም በቅርቢቱ ዓለም ሰጠነው፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከደጋጎቹ ነው፡፡
Verse 28
ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ) «እናንተ ጠያፍን ስራ ትሠራላችሁን በእርሷ ከዓለማት አንድም አልቀደማችሁም፡፡
Verse 29
«እናንተ በእርግጥ ወንዶችን ትመጣላችሁን መንገድንም ትቆርጣላችሁን በሸንጓችሁም የሚነወርን ነገር ትሠራላችሁን» (አላቸው)፡፡ የሕዝቦቹም መልስ «ከእውነተኞቹ እንደ ሆንክ የአላህን ቅጣት አምጣብን» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡
Verse 30
ﯱﯲﯳﯴﯵﯶ
ﯷ
«ጌታዬ ሆይ! በአመጸኞች ሕዝቦች ላይ እርዳኝ» አለ፡፡
Verse 31
መልክተኞቻችንም ኢብራሂምን በብስራት በመጡት ጊዜ «እኛ የዚህችን ከተማ ሰዎች አጥፊዎች ነን፡፡ ሰዎቿ በዳዮች ነበሩና» አሉት፡፡
Verse 32
«በእርሷ ውስጥ ሉጥ አለ እኮ» አላቸው፡፡ «እኛ በውስጧ ያለውን ይበልጥ ዐዋቂ ነን፡፡ (እርሱን) በእርግጥ እናድነዋለን፡፡ ቤተሰቦቹንም ጭምር፡፡ ሚስቱ ብቻ ስትቀር፡፡ እርሷ በጥፋቱ ውስጥ ከሚቀሩት ናት» አሉት፡፡
Verse 33
መልክተኞቻችንም ሉጥን በመጡት ጊዜ በእነሱ ምክንያት አዘነ፡፡ በእነርሱም ልቡ ተጨነቀ፡፡ «አትፍራ፤ አትዘንም፡፡ እኛ አዳኞችህ ነን፡፡ ቤተሰቦችህንም፤ ሚስትህ ብቻ ስትቀር፡፡ እርሷ በጥፋቱ ውስጥ ከቀሪዎቹ ናት» አሉትም፡፡
Verse 34
«እኛ በዚህች ከተማ ሰዎች ላይ ያምጹ በነበሩት ምክንያት ከሰማይ ቅጣትን አውራጆች ነን፡፡»
Verse 35
በእርግጥም ለሚያስቡ ሰዎች ከእርሷ ግልጽ ምልክትን ተውን (አስቀረን)፡፡
Verse 36
ወደ መድየንም ወንድማቸውን ሹዐይብን (ላክን)፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፣ የመጨረሻውንም ቀን ፍሩ፣ በምድርም ውስጥ የምታጠፉ ሆናችሁ አታበላሹ አላቸውም፡፡
Verse 37
አስተባባሉትም፡፡ የምድር መንቀጥቀጥ ያዘቻቸው፡፡ በሃገራቸውም ውስጥ ተንከፍርረው አነጉ፡፡
Verse 38
ዓድንና ሰሙድንም (አጠፋን)፡፡ ከመኖሪያዎቻቸውም (ፍርስራሾች በኩል መጥፋታቸው) ለእናንተ በእውነት ተገለጠላችሁ፡፡ ሰይጣንም ሥራዎቻቸውን ለእነርሱ ሸለመላቸው፡፡ ከመንገድም አገዳቸው፡፡ የማስተዋልም ባለቤቶች ነበሩ፤ (ግን አላስተዋሉም)፡፡
Verse 39
ቃሩንንም ፈርዖንንም ሃማንንም (አጠፋን)፡፡ ሙሳም በተዓምራቶች በእርግጥ መጣባቸው፡፡ በምድርም ላይ ኮሩ፡፡ አምላጪዎችም አልነበሩም፡፡
Verse 40
ሁሉንም በኅጢኣቱ ያዝነው፡፡ ከእነሱም ውስጥ ጠጠርን ያዘለ ነፋስን የላክንበት አልለ፡፡ ከእነሱም ውስጥ ጩኸት የያዘችው አልለ፡፡ ከእነርሱም ውስጥ በእርሱ ምድርን የደረባንበት አልለ፡፡ ከእነሱም ውስጥ ያሰጠምንው አልለ፡፡ አላህም የሚበድላቸው አልነበረም፡፡ ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ፡፡
Verse 41
የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን (ጣዖታትን) የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች ሸረሪት ብጤ ነው፡፡ ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡ ቢያውቁ ኖሮ (አማልክት አድርገው አይግገዟቸውም ነበር)፡፡
Verse 42
አላህ ያንን ከእርሱ ሌላ የሚግገዙትን ማንኛውንም ያውቃል፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡
Verse 43
እነዚህንም ምሳሌዎች ለሰዎች እንገልጻቸዋለን፡፡ ከሊቃውንቶቹም በስተቀር ሌሎቹ አያውቋትም፡፡
Verse 44
«አላህ ሰማያትንና ምድርን እውነተኛ ሆኖ ፈጠረ፡፡» በዚህ ውስጥ ለምእምናን ተዓምር አለበት፡፡
Verse 45
ከመጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፡፡ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀህ ስገድ፡፡ ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና፡፡ አላህንም ማውሳት ከሁሉ ነገር በላጭ ነው፤ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃል፡፡
Verse 46
የመጽሐፉን ባለቤቶችም በዚያች እርሷ መልካም በኾነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ፡፡ ከእነርሱ እነዚያን የበደሉትን ሲቀር፡፡ በሉም «በዚያ ወደኛ በተወረደው ወደናንተም በተወረደው አመንን፡፡ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን፡፡»
Verse 47
እንደዚሁም ወዳንተ መጽሐፍን አወረድን፡፡ እነዚያም መጽሐፍን የሰጠናቸው፤ በእርሱ ያምናሉ፡፡ ከእነዚህም (ከመካ ሰዎች) በእርሱ የሚያምኑ አልሉ፡፡ በተዓምራቶቻችንም ከሓዲዎቹ እንጂ ማንም አይክድም፡፡
Verse 48
ከእርሱ በፊትም መጽሐፍን የምታነብ በቀኝህም የምትጽፈው አልነበርክም፡፡ ያን ጊዜ አጥፊዎቹ በእርግጥ በተጠራጠሩ ነበር፡፡
Verse 49
አይደለም እርሱ (ቁርኣን) በእነዚያ ዕውቀትን በተሰጡት ሰዎች ልቦች ውስጥ (የጠለቀ) ግልጾች አንቀጾች ነው፡፡ በአንቀጾቻችንም በዳዮቹ እንጂ ሌላው አይክድም፡፡
Verse 50
«በእርሱ ላይም ከጌታህ ዘንድ ተዓምራቶች ለምን አልተወረዱም» አሉ፡፡ «ተዓምራቶች አላህ ዘንድ ብቻ ናቸው፡፡ እኔም ግልጽ አስፈራሪ ብቻ ነኝ» በላቸው፡፡
Verse 51
እኛ መጽሐፉን በእነሱ ላይ የሚነበብ ኾኖ ባንተ ላይ ማውረዳችን አይበቃቸውምን በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች ችሮታና ግሳጼ አለበት፡፡
Verse 52
«በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ በአላህ በቃ፡፡ በሰማያትና በምድርም ያለውን ሁሉ ያውቃል» በላቸው፡፡ እነዚያም በብላሽ ነገር ያመኑ በአላህም የካዱ እነዚያ እነሱ ከሳሪዎች ናቸው፡፡
Verse 53
በቅጣትም ያስቸኩሉሃል፡፡ የተወሰነም ጊዜ ባልነበረ ኖሮ ቅጣቱ በመጣባቸው ነበር፡፡ እነርሱ የማያውቁ ሲኾኑም በድንገት በእርግጥ ይመጣባቸዋል፡፡
Verse 54
ﭟﭠﭡﭢﭣﭤ
ﭥ
በቅጣት ያስቸኩሉሃል፡፡ ገሀነምም ከሓዲዎችን በእርግጥ ከባቢ ናት፡፡
Verse 55
ቅጣቱ ከበላያቸው፣ ከእግሮቻቸውም ሥር በሚሸፍናቸው ቀን ትሠሩት የነበራችሁትን ቅመሱ በሚላቸውም (ቀን ትከባቸዋለች)፡፡
Verse 56
እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ (ብትቸገሩ ተሰደዱ)፡፡ እኔንም ብቻ ተገዙኝ፡፡
Verse 57
ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ከዚያም ወደኛ ትመለሳላችሁ፡፡
Verse 58
እነዚያም ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ከገነት በሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ሰገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ በእርግጥ እናሰፍራቸዋለን፡፡ የሠራተኞች ምንዳ ምንኛ አማረ!
Verse 59
ﮙﮚﮛﮜﮝ
ﮞ
(እነሱ) እነዚያ የታገሱ በጌታቸውም ላይ የሚመኩ ናቸው፡፡
Verse 60
ከተንቀሳቃሽም ምግቧን ለመሸከም የማትችለው ብዙ ናት፡፡ አላህ ይመግባታል፡፡ እናንተንም (ይመግባል)፡፡ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡
Verse 61
ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ ማን እንደኾነ ብትጠይቃቸው «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ ታድያ እንዴት ይመለሳሉ፡፡
Verse 62
አላህ ከባሮቹ ለሚሻው ሲሳይን ያሰፋል፡፡ ለእርሱም ያጠብባል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡
Verse 63
ከሰማይም ውሃን ያወረደና በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው ያደረጋት ማን እንደኾነ ብትጠይቃቸው «አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ምስጋና ለአላህ ነው» በላቸው፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡
Verse 64
ይህችም የቅርቢቱ ሕይወት መታለያና ጨዋታ እንጂ ሌላ አይደለችም፡፡ የመጨረሻይቱም አገር እርሷ በእርግጥ የዘላለም ሕይወት አገር ናት፡፡ የሚያውቁ ቢኾኑ ኖሮ፤ (ጠፊይቱን ሕይወት አይመርጡም ነበር)፡፡
Verse 65
በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም አላህን መገዛትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ኾነው ይጠሩታል፡፡ ወደ የብስ (በማውጣት) ባዳናቸው ጊዜም ወዲያውኑ እነርሱ (ጣዖትን) ያጋራሉ፡፡
Verse 66
በሰጠናቸው ጸጋ ሊክዱና ሊጠቃቀሙ (ያጋራሉ)፡፡ ወደፊትም (የሚጠብቃቸውን) ያውቃሉ፡፡
Verse 67
ሰዎቹ ከዙሪያቸው ሲነጠቁ እኛ (አገራቸውን ) ጸጥተኛ ክልል ማድረጋችንን አያዩምን በውድቅ ነገር ያምናሉን በአላህም ጸጋ ይክዳሉን
Verse 68
በአላህ ላይም ውሸትን ከቀጣጠፈ ሰው ወይም እውነቱ በመጣለት ጊዜ ከአስዋሸ ይበልጥ በዳይ ማነው በገሀነም ውስጥ ለከሓዲዎች መኖሪያ የለምን
Verse 69
እነዚያም በእኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን፡፡ አላህም በእርግጥ ከበጎ ሠሪዎች ጋር ነው፡፡
تقدم القراءة