የሱራ الحشر ትርጉም በالأمهرية ከSadiq and Sani - Amharic translation
Verse 1
በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ ለአላህ አሞገሰ፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡
እርሱ ያ ከመጽሐፉ ሰዎች እነዚያን የካዱትን ከቤቶቻቸው ለመጀመሪያው ማውጣት ያወጣቸው ነው፡፡ መውጣታቸውን አላሰባችሁም፡፡ እነርሱም ምሽጎቻቸው ከአላህ (ኀይል) የሚከላከሉላቸው መኾናቸውን አሰቡ፡፡ አላህም ካላሰቡት ስፍራ መጣባቸው፡፡ በልቦቻቸውም ውስጥ መርበድበድን ጣለባቸው፡፡ ቤቶቻቸውን በእጆቻቸውና በምእምናኖቹ እጆች ያፈርሳሉ፡፡ አስተውሉም የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ!
Verse 3
በእነርሱም ላይ አላህ ከአገር መውጣትን ባልጻፈ ኖሮ በቅርቢቱ ዓለም በቀጣቸው ነበር፡፡ ለእነርሱም በመጨረሻይቱ (ዓለም) የእሳት ቅጣት አልላቸው፡፡
Verse 4
ይህ እነርሱ አላህንና መልክተኛውን በመከራከራቸው ነው፡፡ አላህንም የሚከራከር ሰው (ይቀጣዋል)፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡
Verse 5
ከዘንባባ (ከተምር ዛፍ) ማንኛዋም የቆረጣችኋት ወይም በግንዶቿ ላይ የቆመች ኾና የተዋችኋት በአላህ ፈቃድ ነው፡፡ አመጸኞቸንም ያዋርድ ዘንድ (በመቁረጥ ፈቀደ)፡፡
Verse 6
ከእነርሱም (ገንዘብ) በመልእክተኛው ላይ አላህ የመለሰው በእርሱ ላይ ፈረሶችንና ግመሎችን አላስጋለባችሁበትም፡፡ ግን አላህ መልክተኞቹን በሚሻው ሰው ላይ ይሾማል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡
አላህ ከከተሞቹ ሰዎች (ሀብት) በመልክተኛው ላይ የመለሰው (ሀብት) ከእናንተ ውስጥ በሀብታሞቹ መካከል ተዘዋዋሪ እንዳይኾን፡፡ ለአላህና ለመልክተኛው፣ ለዝምድና ባለቤትም፣ አባት ለሌላቸው ልጆችም፣ ለድኾችም፣ ለመንገደኛም (የሚስሰጥ) ነው፡፡ መልክተኛውም የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡
Verse 8
ለእነዚያ የአላህን ችሮታና ውዴታውን የሚፈልጉ፣ አላህንና መልክተኛውንም የሚረዱ ኾነው ከአገሮቻቸውና ከገንዘቦቻቸው ለተወጡት ስደተኞች ድኾች (ይስሰጣል)፡፡ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው፡፡
Verse 9
እነዚያም ከበፊታቸው አገሪቱን መኖሪያ ያደረጉት እምነትንም የለመዱት ወደእነርሱ የተሰደዱትን ሰዎች ይወዳሉ፡፡ (ስደተኞቹ) ከተሰጡትም ነገር በልቦቻቸው ውስጥ ቅሬታን አያገኙም፡፡ በእነርሱ ላይ ችግር ቢኖርባቸውም በነፍሶቻቸው ላይ ሌላውን ይመርጣሉ፡፡ የነፍሱንም ንፍገት የሚጠበቅ ሰው እነዚያ እነሱ ምኞታቸውን አግኚዎች ናቸው፡፡
Verse 10
እነዚያም ከበኋላቸው የመጡት «ጌታችን ሆይ! ለእኛም ለእነዚያም በእምነት ለቀደሙን ወንድሞቻችን ምሕረት አድርግ፡፡ በልቦቻችንም ውስጥ ለእነዚያ ለአመኑት (ሰዎች) ጥላቻን አታድርግ፡፡ ጌታችን ሆይ! አንተ ርኅሩህ አዛኝ ነህና» ይላሉ፡፡
Verse 11
ወደእነዚያ ወደ ነፈቁት አላየህምን? ከመጽሐፉ ሰዎች ውስጥ ለእነዚያ ለካዱት ወንድሞቻቸው (ከአገር) «ብትባረሩ አብረናችሁ እንወጣለን፡፡ በእናንተም (ጉዳይ) አንድንም በፍጹም አንታዘዝም፡፡ ብትገድሉም በእርግጥ እንረዳችኋለን» ይሏቸዋል፡፡ አላህም እነርሱ ውሸታሞች መኾናቸውን ይመሰክራል፡፡
Verse 12
ቢወጥጡ አብረዋቸው አይወጡም፤ ቢገደሉም አይረዱዋቸውም፡፡ ቢረዷቸውም (ለሽሽት) ጀርባቸውን ያዞራሉ፡፡ ከዚያም እርዳታን አያገኙም፡፡
Verse 13
እናንተ በልቦቻቸው ውስጥ በማስፈራት ከአላህ ይልቅ የበረታችሁ ናችሁ፡፡ ይህ እነርሱ የማያውቁ ሕዝቦች በመኾናቸው ነው፡፡
Verse 14
በተመሸጉ ከተሞች ውስጥ ወይም ከአጥሮች ጀርባ ኾነው እንጅ፤ የተሰበሰቡ ኾነው አይዋጉዋችሁም፡፡ ኀይላቸው በመካከላቸው ብርቱ ነው፡፡ ልቦቻቸው የተበታተኑ ሲኾኑ የተሰበሰቡ ናቸው ብለህ ትጠረጥራቸዋለህ፡፡ ይህ እነሱ አእምሮ የሌላቸው ሕዝቦች በመኾናቸው ነው፡፡
Verse 15
(ብጤያቸው) እንደእነዚያ ከእነሱ በፊት በቅርብ ጊዜ የነገራቸውን ቅጣት እንደቀመሱት ብጤ ነው፡፡ ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡
Verse 16
እንደ ሰይጣን ብጤ ለሰውየው «ካድ» ባለው ጊዜና በካደም ጊዜ «እኔ ከአንተ ንጹሕ ነኝ እኔ አላህን የዓለማትን ጌታ እፈራለሁ» እንዳለው ነው፡፡
Verse 17
መጨረሻቸውም እነርሱ በውስጡ ዘውታሪዎች ሲኾኑ በእሳት ውስጥ መኾን ነው፡፡ ይህም የበዳዮች ዋጋ ነው፡፡
Verse 18
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን ትመልከት፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡
Verse 19
እንደነዚያም አላህን እንደረሱትና ነፍሶቻቸውን እንዳስረሳቸው (ሰዎች) አትኹኑ፡፡ እነዚያ እነርሱ አመጸኞቹ ናቸው፡፡
Verse 20
የእሳት ጓዶችና የገነት ጓዶች አይተካከሉም፡፡ የገነት ጓዶች እነርሱ ምኞታቸውን አግኚዎች ናቸው፡፡
Verse 21
ይህንን ቁርኣን በተራራ ላይ ባወረድነው ኖሮ ከአላህ ፍራቻ (የተነሳ) ተዋራጅ ተሰንጣቂ ኾኖ ባየኸው ነበር፡፡ ይህችንም ምሳሌ ይገመግሙ ዘንድ ለሰዎች እንገልፃለን፡፡
Verse 22
እርሱ አላህ ነው፤ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ የኾነ ነው፡፡ እርሱ እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ ነው፡፡
Verse 23
እርሱ አላህ ነው፡፡ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ ከጉድለት ሁሉ የጠራው፣ የሰላም ባለቤቱ፣ ጸጥታን ሰጪው፣ ባሮቹን ጠባቂው፣ አሸናፊው፣ ኀያሉ፣ ኩሩው ነው፡፡ አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፡፡
Verse 24
እርሱ አላህ ፈጣሪው (ከኢምንት) አስገኚው፣ ቅርጽን አሳማሪው ነው፡፡ ለእርሱ መልካሞች ስሞች አልሉት፡፡ በሰማያትና በምድርም ያለው ሁሉ ለእርሱ ያሞግሳል፡፡ እርሱም
تقدم القراءة