የሱራ النّور ትርጉም በالأمهرية ከSadiq and Sani - Amharic translation
Verse 1
(ይህች) ያወረድናትና የደነገግናት ምዕራፍ ናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ትገሰፁ ዘንድ ግልጾችን አንቀጾች አውርደናል፡፡
Verse 2
ዝሙተኛይቱና ዝሙተኛው ከሁለቱ እያንዳንዳቸውን (ያላገቡ እንደኾኑ) መቶ ግርፋትን ግረፉዋቸው፤ በእነርሱም በአላህ ፍርድ ርኅራኄ አትያዛችሁ፡፡ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ እንደኾናችሁ (አትራሩ)፡፡ ቅጣታቸውንም ከምእምናን ጭፍሮች ይገኙበት፡፡
Verse 3
ዝሙተኛው ዝሙተኛይቱን ወይም አጋሪይቱን እንጂ አያገባም፡፡ ዝሙተኛይቱንም ዝሙተኛ ወይም አጋሪ እንጂ አያገባትም፡፡ ይህም በምእምናን ላይ ተከልክሏል፡፡
Verse 4
እነዚያም ጥብቆችን ሴቶች (በዝሙት) የሚሰድቡ ከዚያም አራትን ምስክሮች ያላመጡ ሰማኒያን ግርፋት ግረፏቸው፡፡ ከእነርሱም ምስክርነትን ሁልጊዜ አትቀበሉ እነዚያም እነሱ አመጸኞች ናቸው፡፡
Verse 5
እነዚያ ከዚህ በኋላ የተጸጸቱና ሥራቸውን ያሳመሩ ሲቀሩ፡፡ አላህ በጣም መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
Verse 6
እነዚያም ሚስቶቻቸውን (በዝሙት) የሚሰድቡ ለእነሱም ከነፍሶቻቸው በስተቀር ምስክሮች የሌሏቸው የኾኑ የአንዳቸው ምስክርነት እርሱ ከውነተኞች ለመኾኑ በአላህ ስም አራት ጊዜ ምሎ መመስከር ነው፡፡
Verse 7
አምስተኛይቱም ከውሸታሞች ቢኾን በእርሱ ላይ የአላህ እርግማን ይኑርበት (ብሎ መመስከር) ነው፡፡
Verse 8
እርሱም ከውሸታሞች ነው ብላ አራት ጊዜ መመስከሮችን በአላህ ስም መመስከርዋ ከእርስዋ ላይ ቅጣትን ይገፈትርላታል፡፡
Verse 9
አምስተኛይቱም እርሱ ከውነተኞች ቢኾን በእርስዋ ላይ የአላህ ቁጣ ይኑርባት (ብላ መመስከርዋ) ነው፡፡
Verse 10
በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ አላህም ጸጸትን ተቀባይ ጥበበኛ ባልኾነ ኖሮ (ውሸታሙን ይገልጸው ነበር)፡፡
Verse 11
እነዚያ መጥፎን ውሸት ያመጡ ከናንተው የኾኑ ጭፍሮች ናቸው፡፡ ለእናንተ ክፉ ነገር ነው ብላችሁ አታስቡት፡፡ በእውነቱ እርሱ ለእናንተ መልካም ነገር ነው፡፡ ከእነርሱ (ከጭፍሮቹ) ለያንዳንዱ ሰው ከኀጢአት የሠራው ሥራ ዋጋ አለው፡፡ ያም ከእነሱ ትልቁን ኀጢአት የተሸከመው ለእርሱ ከባድ ቅጣት አለው፡፡
Verse 12
(ውሸቱን) በሰማችሁት ጊዜ ምእምናንና ምእምናት በጎሶቻቸው ለምን ደግን ነገር አልጠረጠሩም ለምንስ ይህ ግልጽ ውሸት ነው አላሉም
Verse 13
በእርሱ ላይ ለምን አራትን ምስክሮች አላመጡም ምስክሮቹንም ካላመጡ እነዚያ አላህ ዘንድ ውሸታሞቹ እነሱ ናቸው፡፡
Verse 14
በቅርቢቱም በመጨረሻይቱም ዓለም በእናንተ ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ በውስጡ በገባችሁበት ወሬ ምክንያት ታላቅ ቅጣት በእርግጥ በደረሰባችሁ ነበር፡፡
Verse 15
በምላሶቻችሁ በምትቅበባሉት ጊዜ ለእናንተም በእርሱ ዕውቀት በሌላችሁ ነገር በአፎቻችሁ በተናገራችሁና እርሱ አላህ ዘንድ ከባድ ኀጢአት ኾኖ ሳለ ቀላል አድርጋችሁ ባሰባችሁት ጊዜ (ከባድ ቅጣት በነካችሁ ነበር)፡፡
Verse 16
በሰማችሁትም ጊዜ በዚህ ልንናገር ለእኛ አይገባንም፡፡ ጥራት ይገባህ፡፡ ይህ ከባድ ቅጥፈት ነው፤ አትሉም ነበርን
Verse 17
ምእመናን እንደኾናችሁ ወደ ብጤው በፍፁም እንዳትመለሱ አላህ ይገስጻችኋል፡፡
Verse 18
ለእናንተም አላህ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡
Verse 19
እነዚያ በእነዚያ ባመኑት ሰዎች ውስጥ መጥፎ ወሬ እንድትስፋፋ የሚወዱ ለእነሱ በቅርቢቱም በመጨረሻይቱም ዓለም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡ አላህም ያውቃል እናንተ ግን አታውቁም፡፡
Verse 20
በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታውና እዝነቱ ባልነበረ አላህም ሩኅሩኅና አዛኝ ባልኾነ ኖሮ (ቶሎ ባጠፋችሁ ነበር)፡፡
Verse 21
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሰይጣንን እርምጃዎች አትከተሉ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች የሚከተል ሰው (ኀጢአትን ተሸከመ)፡፡ እርሱ በመጥፎና በሚጠላ ነገር ያዛልና፡፡ በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ ከናንተ አንድም ፈጽሞ ባልጠራ ነበር፡፡ ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያጠራል፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡
Verse 22
ከእናንተም የችሮታና የክብረት ባለቤቶች የኾኑት ለቅርብ ዘመዶችና ለድኾች በአላህም መንገድ ለተሰደዱ ሰዎች ላይሰጡ አይማሉ፡፡ ይቅርታም ያድርጉ፡፡ (ጥፋተኞቹን) ይለፉም፡፡ አላህ ለእናንተ ሊምር አትወዱምን አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
Verse 23
እነዚያ ጥብቆቹን ከዝሙት ዘንጊዎቹን ምእምናት የሚሰድቡ፤ በቅርቢቱም በመጨረሻይቱም ዓለም ተረገሙ፡፡ ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አላቸው፡፡
Verse 24
በእነሱ ላይ ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ነገር በሚመሰክሩባቸው ቀን (ከባድ ቅጣት አላቸው)፡፡
Verse 25
በዚያ ቀን አላህ እውነተኛ ዋጋቸውን ይሞላላቸዋል፡፡ አላህም እርሱ መኖሩ የተረጋገጠ (ሁሉን ነገር) ገላጭ መኾኑን ያውቃሉ፡፡
Verse 26
መጥፎዎቹ ሴቶች ለመጥፎዎች ወንዶች መጥፎዎቹ ወንዶችም ለመጥፎዎቹ ሴቶች የተገቡ ናቸው፡፡ ጥሩዎቹ ሴቶችም ለጥሩዎቹ ወንዶች ጥሩዎቹ ወንዶችም ለጥሩዎቹ ሴቶች የሚገቡ ናቸው፡፡ እነዚያ (መጥፎዎቹ) ከሚሉት ነገር ንጹሕ የተደረጉ ናቸው፡፡ ለእነርሱ ምህረትና መልካም ሲሳይ አላቸው፡፡
Verse 27
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እስከምታስፈቅዱና በባለቤቶቿ ላይ ሰላምታን እስከምታቀርቡ ድረስ ከቤቶቻችሁ ሌላ የኾኑን ቤቶች አትግቡ፡፡ ይህ ለእናንተ መልካም ነው፡፡ እናንተ ትገነዘቡ ዘንድ (በዚህ ታዘዛችሁ)፡፡
Verse 28
በውስጧም አንድንም ሰው ባታገኙ ለእናንተ እስከሚፈቀድላችሁ ድረስ አትግቧት፡፡ ለእናንተ ተመለሱ ብትባሉም ተመለሱ፡፡ እርሱ ለእናንተ የተሻለ ነው፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
Verse 29
መኖሪያ ያልኾኑን ቤቶች በውስጣቸው ለእናንተ ጥቅም ያላችሁን (ሳታስፈቅዱ) ብትገቡ በእናንተ ላይ ኀጢአት የለባችሁም፡፡ አላህም የምትገልጹትንና የምትደብቁትን ሁሉ ያውቃል፡፡
Verse 30
ለምእመናን ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን (ያልተፈቀደን ከማየት) ይከልክሉ፤ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፤ ይህ ለነሱ የተሻለ ነው፤ አላህ በሚሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡
ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡ ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ፡፡ (የውስጥ) ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ወይም ለወንዶች ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለወንድሞቻቸው ወይም ለወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለእህቶቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለሴቶቻቸው ወይም እጆቻቸው ለያዙት (ባሪያ) ወይም ከወንዶች ለሴት ጉዳይ የሌላቸው ለኾኑ ተከታዮች ወይም ለነዚያ በሴቶች ሐፍረተ ገላ ላይ ላላወቁ ሕፃኖች ካልኾነ በስተቀር አይግለጹ፡፡ ከጌጣቸውም የሚሸፍኑት ይታወቅ ዘንድ በእግሮቻቸው አይምቱ፡፡ ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ፡፡
Verse 32
ከናንተም ትዳር የሌላቸውን አጋቡ፡፡ ከወንዶች ባሮቻችሁና ከሴቶች ባሮቻችሁም ለጋብቻ ብቁ የኾኑትን (አጋቡ)፡፡ ድኾች ቢኾኑ አላህ ከችሮታው ያከብራቸዋል፡፡ አላህም ስጦታው ሰፊ ዐዋቂ ነው፡፡
እነዚያም የማግቢያን ጣጣ የማያገኙ አላህ ከችሮታው እስከሚያከብራቸው ድረስ ይጠበቁ፡፡ እነዚያንም እጆቻችሁ ከጨበጧቸው አገልጋዮች (ገንዘብ ሰጥተው ነጻ ለመውጣት) መጻጻፍን የሚፈልጉትን ከእነሱ መልካምን ነገር ብታውቁ ተጻጻፉዋቸው፡፡ ከአላህም ገንዘብ ከዚያ ከሰጣችሁ ስጧቸው፡፡ ሴቶች ባሮቻችሁንም መጥጠበቅን ቢፈልጉ የቅርቢቱን ሕይወት ጥቅም ለመፈለግ ብላችሁ በዝሙት ላይ አታስገድዱዋቸው፡፡ የሚያስገድዳቸውም ሰው አላህ ከመገደዳቸው በኋላ (ለተገደዱት) መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
Verse 34
ወደእናንተም አብራሪ የኾኑን አንቀጾች ከእነዚያ ከበፊታችሁ ካለፉትም (ምሳሌዎች ዓይነት) ምሳሌን ለጥንቁቆቹ መገሰጫንም በእርግጥ አወረድን፡፡
አላህ የሰማያትና የምድር አብሪ ነው፡፡ የብርሃኑ ምሳሌ በውስጧ መብራት እንዳለባት (ዝግ) መስኮት፣ መብራቱ በብርጭቆ ውስጥ የኾነ፣ ብርጭቆይቱ ፍፁም ሉላዊ ኮከብ የምትመሰል፣ ምሥራቃዊው ምዕራባዊም ካልኾነች ከተባረከች የወይራ ዛፍ ዘይቷ እሳት ባይነካውም እንኳ ሊያበራ የሚቀርብ ከኾነች (ዘይት) የሚቃጠል እንደ ሆነ (መብራት) ነው፡፡ (ይህ) በብርሃን ላይ የኾነ ብርሃን ነው፡፡ አላህ ወደ ብርሃኑ የሚሻውን ሰው ይመራል፡፡ አላህም ለሰዎች ምሳሌዎችን ያቀርባል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
Verse 36
አላህ እንድትከበርና ስሙ በውስጧ እንዲወሳ ባዘዘው ቤቶች ውስጥ (አወድሱት)፡፡ በውስጧ በጧትና በማታ ለእርሱ ያጠራሉ፡፡
Verse 37
አላህን ከማውሳትና ሶላትን ከመስገድ ዘካንም ከመስጠት ንግድም ሽያጭም የማያታልላቸው ልቦችና ዓይኖች በእርሱ የሚገላበጡበትን ቀን የሚፈሩ የኾኑ ሰዎች (ያጠሩታል)፡፡
Verse 38
አላህ የሠሩትን ሥራ መልካሙን ሊመነዳቸው ከችሮታውም ሊጨመርላቸው (ያጠሩታል)፡፡ አላህም ለሚሻው ሰው ያለ ግምት ይሰጣል፡፡
Verse 39
እነዚያም የካዱት ሰዎች ሥራዎቻቸው (መልካሞቹ) በበረሃ ሜዳ እንዳለ ሲሪብዱ የጠማው ሰው ውሃ ነው ብሎ እንደሚያስበው በመጣውም ጊዜ ምንም ነገር ኾኖ እንደማያገኘው ነው፡፡ (ከሓዲው) አላህንም እሠራው ዘንድ ያገኘዋል፡፡ ምርመራውንም (ቅጣቱን) ይሞላለታል፡፡ አላህም ምርመራው ፈጣን ነው፡፡
Verse 40
ወይም (መጥፎ ሥራዎቻቸውን) ከበላዩ ደመና ያለበት ማዕበል በሚሸፈነው ጥልቅ ባህር ውስጥ እንዳሉ ጨለማዎች ነው፡፡ (እነዚያ) ከፊላቸው ከከፊሉ በላይ ድርብርብ የኾኑ ጨለማዎች ናቸው፡፡ (በዚህች) የተሞከረ (ሰው) እጁን ባወጣ ጊዜ ሊያያት አይቀርብም፡፡ አላህም ለእርሱ ብርሃንን ያላደረገለት ሰው ለእርሱ ምንም ብርሃን የለውም፡፡
Verse 41
አላህ በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ በራሪዎችም ክንፎቻቸውን (በአየር ላይ) ያንሳፈፉ ኾነው ለእርሱ የሚያጠሩ (የሚያወድሱ) መኾናቸውን አላወቅህምን ሁሉም ስግደቱንና ማጥራቱን በእርግጥ ዐወቀ፡፡ አላህም የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
Verse 42
የሰማያትና የምድርም ግዛት የአላህ ነው፡፡ መመለሻም ወደ አላህ ነው፡፡
Verse 43
አላህ ደመናን የሚነዳ መኾኑን አላየህምን ከዚያም ከፊሉን ከከፊሉ ያገናኛል፡፡ ከዚያም የተደራረበ ያደርገዋል፡፡ ዝናቡንም ከመካከሉ የሚወጣ ኾኖ ታየዋለህ፡፡ ከሰማይም (ከደመና) በውስጧ ካሉት ጋራዎች በረዶን ያወርዳል፡፡ በእርሱም የሚሻውን ሰው (በጉዳት) ይነካል፡፡ ከሚሻውም ሰው ላይ ይመልሰዋል፡፡ የብልጭታው ብርሃን ዓይኖችን ሊወስድ ይቀርባል፡፡
Verse 44
አላህ ሌሊትንና ቀንን ያገላብጣል፡፡ በዚህም ለባለ ውስጥ ዓይኖች በእርግጥ ማስረጃ አልለበት፡፡
Verse 45
አላህም ተንቀሳቃሽን ሁሉ ከውሃ ፈጠረ፡፡ ከእነሱም በሆዱ ላይ የሚኼድ አልለ፡፡ ከእነሱም በሁለት እግሮች ላይ የሚኼድ አልለ፡፡ አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡
Verse 46
አብራሪን አንቀጾች በእርግጥ አወረድን፡፡ አላህም የሚሻውን ሰው ወደ ቀጥተኛ መንገድ ይመራዋል፡፡
Verse 47
በአላህና በመልክተኛውም አምነናል ታዘናልም ይላሉ፡፡ ከዚያም ከዚህ በኋላ ከእነሱ ከፊሉ ይሸሻል፡፡ እነዚያም ምእምናን አይደሉም፤
Verse 48
ወደ አላህና ወደ መልክተኛውም በመካከላቸው ሊፈርድ በተጠሩ ጊዜ ከእነሱ ከፊሉ ወዲያውኑ ይሸሻሉ፡፡
Verse 49
እውነቱም (ሐቁ) ለእነሱ ቢኾን ወደርሱ ታዛዦች ኾነው ይመጣሉ፡፡
Verse 50
በልቦቻቸው ውስጥ በሺታ አለን ወይስ (በነቢይነቱ) ተጠራጠሩን ወይስ አላህና መልክተኛው በእነሱ ላይ የሚበድሉ መኾንን ይፈራሉን ይልቁንም፤ እነዚያ እነሱ በዳዮቹ ናቸው፡፡
Verse 51
የምእምናን ቃል የነበረው ወደ አላህና ወደ መልክተኛው በመካከላቸው ሊፈርድ በተጠሩ ጊዜ ሰማን፤ ታዘዝንም ማለት ብቻ ነው፡፡ እነዚህም እነሱ የፈለጉትን የሚያገኙ ናቸው፡፡
Verse 52
አላህንና መልክተኛውን የሚታዘዝም ሰው፣ አላህንም የሚፈራና የሚጠነቀቀው ሰው፤ እነዚያ እነርሱ ፍለጎታቸውን የሚያገኙ ናቸው፡፡
Verse 53
(ለዘመቻ) ብታዛቸውም በእርግጥ ሊወጡ የጠነከሩ መሓሎቻቸውን በአላህ ስም ይምላሉ፡፡ «አትማሉ፤ የታወቀች (የንፍቅና) መታዘዝ ናትና፡፡ አላህ በምትሠሩት ነገር ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡
Verse 54
«አላህን ተገዙ፡፡ መልክተኛውንም ታዘዙ፤ ብትሸሹም (አትጎዱትም)፡፡ በእርሱ ላይ ያለበት የተገደደውን ማድረስ ብቻ ነው፡፡ በእናንተም ላይ ያለባችሁ የተገደዳችሁት (መታዘዝ) ብቻ ነው፡፡ ብትታዘዙትም ትምመራላችሁ፡፡ በመልእክተኛውም ላይ ግልጽ ማድረስ እንጂ ሌላ የለበትም» በላቸው፡፡
Verse 55
አላህ እነዚያን ከእናንተ ያመኑትንና መልካም ሥራዎችን የሠሩትን እነዚያን ከእነሱ በፊት የነበሩትን እንደተካ በምድር ለይ በእርግጥ ሊተካቸው፣ ለእነሱም ያንን የወደደላቸውን ሃይማኖታቸውን ሊያደላድልላቸው፣ ከፍርሃታቸውም በኋላ ጸጥታን ሊለውጥላቸው ተስፋን ቃል ሰጥቷቸዋል፡፡ በእኔ ምንንም የማያጋሩ ኾነው ይግገዙኛል፡፡ ከዚያም በኋላ የካደ ሰው እነዚያ እነርሱ አመጸኞች ናቸው፡፡
Verse 56
ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፡፡ ምጽዋትንም ስጡ፡፡ መልክተኛውንም ታዘዙ፡፡ ለእናንተ ሊታዘንላችሁ ይከጀላልና፡፡
Verse 57
እነዚያን የካዱትን በምድር ውስጥ የሚያቅቱ አድርገህ አታስብ፡፡ መኖሪያቸውም እሳት ናት፡፡ በእርግጥም የከፋች መመለሻ ናት፡፡
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያ እጆቻችሁ የጨበጧቸው (ባሮች) እነዚያም ከእናንተ ለአካላ መጠን ያልደረሱት ከጎህ ስግደት በፊት፣ በቀትርም ልብሶቻችሁን በምታወልቁ ጊዜ ከምሽት ስግደትም በኋላ ሦስት ጊዜያት (ለመግባት ሲፈልጉ) ያስፈቅዷችሁ፡፡ (እነዚህ) ለእናንተ የኾኑ ሦስት የሐፍረተ ገላ መገለጫ ጊዜያቶች ናቸውና፡፡ ከእነዚህ በኋላ በእናንተም በእነርሱም ላይ (ያለፈቃድ በመግባት) ኀጢአት የለም፡፡ በእናንተ ላይ (ለማገልገል) ዙዋሪዎች ናቸውና፡፡ ከፊላችሁ በከፊሉ ላይ ዙዋሪ ነው፡፡ እንደዚሁ አላህ ለእናንተ ሕግጋትን ይገልጽላችኋል፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡
Verse 59
ከእናንተም ሕፃናቶቹ አቅመ አዳምን በደረሱ ጊዜ እነዚያ ከእነሱ በፊት የነበሩት (ታላላቆቹ) እንዳስፈቀዱ ያስፈቅዱ፡፡ እንደዚሁ አላህ ለእናንተ አንቀጾቹን ያብራራል፤ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡
Verse 60
ከሴቶችም እነዚያ ጋብቻን የማይፈልጉት ተቀማጮች (ባልቴቶች)፤ በጌጥ የተገለፁ ሳይኾኑ የላይ ልብሶቻቸውን ቢጥሉ በእነሱ ላይ ኀጢአት የለባቸውም፡፡ ግን መጠበቃቸው ለእነርሱ የተሻለ ነው፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡
(ከሰዎች ጋር በመብላት) በዕውር ላይ ኀጢአት የለበትም፡፡ በአንካሳም ላይ ኀጢአት የለበትም፡፡ በበሽተኛም ላይ ኀጢአት የለበትም፡፡ በነፍሶቻችሁም ላይ ከቤቶቻችሁ ወይም ከአባቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከእናቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከወንድሞቻችሁ ቤቶች ወይም ከእኅቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከአጎቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከአክስቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከየሹሞቻችሁ ቤቶች ወይም ከየሹሜዎቻችሁ ቤቶች ወይም መክፈቻዎቹን ከያዛችሁት ቤት ወይም ከወዳጃችሁ ቤት (ብትበሉ) ኀጢአት የለባችሁም፡፡ ተሰብስባችሁ ወይም ተለያይታችሁ ብትበሉ በእናንተ ላይ ኀጢአት የለባችሁም፡፡ ቤቶችንም በገባችሁ ጊዜ፤ ከአላህ ዘንድ የኾነችን የተባረከች መልካም ሰላምታ በነፍሶቻችሁ ላይ ሰላም በሉ፡፡ እንደዚሁ አላህ አንቀጾችን ለእናንተ ያብራራል፡፡ ልታውቁ ይከጀላልና፡፡
Verse 62
ምእመናን ማለት እነዚያ በአላህና በመልክተኛው ያመኑት፤ ከእርሱ ጋር በሚሰበሰብ ጉዳይ ላይ በኾኑ ጊዜ እስከሚያስፈቅዱ ድረስ የማይኼዱት ብቻ ናቸው፡፡ እነዚያ የሚያስፈቅዱህ እነርሱ እነዚያ በአላህና በመልክተኛው የሚያምኑት ናቸው፡፡ ለግል ጉዳያቸውም ፈቃድ በጠየቁህ ጊዜ ከእነሱ ለሻኸው ሰው ፍቀድለት፡፡ ለእነሱም አላህን ምሕረትን ለምንላቸው አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
Verse 63
በመካከላችሁ የመልክተኛውን ጥሪ ከፊላችሁ ከፊሉን እንደ መጥራት አታድርጉት፡፡ ከእናንተ ውስጥ እነዚያን እየተከለሉ በመስለክለክ የሚወጡትን አላህ በእርግጥ ያውቃቸዋል፡፡ እነዚያም ትዕዛዙን የሚጥሱ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ፡፡
Verse 64
ንቁ! በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ብቻ ነው፡፡ እናንተ በእርሱ ላይ ያላችሁበትን ኹኔታ በእርግጥ ያውቃል፡፡ ወደእርሱ የሚመለሱበትን ቀንም (ያውቃል)፡፡ የሠሩትንም ሁሉ ይነግራቸዋል፡፡ አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
تقدم القراءة