የሱራ النحل ትርጉም በالأمهرية ከSadiq and Sani - Amharic translation
Verse 1
የአላህ ትዕዛዝ መጣ፤ ስለዚህ አታስቸኩሉት፤ ከማይገባው ሁሉ ጠራ ከሚያጋሩትም ሁሉ ላቀ፤
Verse 2
ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል (ከሓዲዎችን በቅጣት) አስጠንቅቁ፤ እነሆ ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ፍሩኝም ማለትን (አስታውቁ በማለት ያወርዳል)፡፡
Verse 3
ሰማያትንና ምድርን በእውነት ፈጠረ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፡፡
Verse 4
ሰውን ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው፡፡ ከዚያም እርሱ ወዲያውኑ (ትንሣኤን በመካድ) ግልጽ ተከራካሪ ይኾናል፡፡
Verse 5
ግመልን፣ ከብትን፣ ፍየልንም በርሷ (ብርድ መከላከያ) ሙቀት ጥቅሞችም ያሉባት ስትኾን ለእናንተ ፈጠረላችሁ፡፡ ከርሷም ትበላላችሁ፡፡
Verse 6
ለእናንተም በእርሷ ወደ ማረፊያዋ በምትመልሷት ጊዜ በምታሰማሩዋትም ጊዜ ውበት አላችሁ፡፡
Verse 7
ጓዞቻችሁንም በነፍሶች ችግር እንጂ ወደማትደርሱበት አገር ትሸከማለች፡፡ ጌታችሁ በእርግጥ ሩኅሩኅ አዛኝ ነውና፡፡
Verse 8
ፈረሶችንም፣ በቅሎዎችንም፣ አህዮችንም ልትቀመጡዋቸውና ልታጌጡባቸው (ፈጠረላችሁ)፡፡ የማታውቁትንም ድንቅ ነገር ይፈጥራል፡፡
Verse 9
በአላህም ላይ (በችሮታው) ቀጥተኛውን መንገድ መግለጽ አለበት፡፡ ከእርሷም (ከመንገድ) ጠማማ አልለ፡፡ በሻም ኖሮ ሁላችሁንም በእርግጥ ባቀናችሁ ነበር፡፡
Verse 10
እርሱ ያ ከሰማይ ውሃን ያወረደ ነው፡፡ ከእርሱ ለእናንተ መጠጥ አላችሁ፡፡ ከእርሱም (እንስሳዎችን) በእርሱ የምታሰማሩበት ዛፍ (ይበቅልበታል)፡፡
Verse 11
በእርሱ ለእናንተ አዝመራን፣ (የዘይት) ወይራንም፣ ዘምባባዎችንም (ተምርን)፣ ወይኖችንም፣ ከፍሬዎችም ሁሉ ያበቅልላችኋል፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምርአልለ፡፡
Verse 12
ለእናንተም ሌሊትንና ቀንን፣ ፀሐይንና ጨረቃንም ገራላችሁ፡፡ ከዋክብትም በፈቃዱ የተገሩ ናቸው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያውቁ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምራቶች አልሉ፡፡
Verse 13
በምድርም ላይ መልኮቹ የተለያዩ ኾኖ ለእናንተ የፈጠረላችሁን ሁሉ (ገራላችሁ)፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚገሰጹ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አልለ፡፡
Verse 14
እርሱም ያ ባሕርን ከእርሱ እርጥብ ስጋን ልትበሉና ከእርሱም የምትለብሱትን ጌጣጌጥ ታወጡ ዘንድ የገራ ነው፡፡ መርከቦችንም በውስጡ (ውሃውን) ቀዳጆች ኾነው (ሲንሻለሉ) ታያለህ፡፡ ከችሮታው ልትፈልጉና ልታመሰግኑም (ገራላችሁ)፡፡
Verse 15
በምድርም ውስጥ በእናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለባት፡፡ ጂረቶችንም፣ መንገዶችንም ትመሩ ዘንድ (አደረገ)፡፡
Verse 16
ﭝﭞﭟﭠﭡ
ﭢ
ምልክቶችንም (አደረገ)፡፡ በከዋክብትም እነሱ ይምመራሉ፡፡
Verse 17
የሚፈጥር እንደማይፈጥር ነውን አትገሰጹምን
Verse 18
የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም፡፡ አላህ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
Verse 19
ﭸﭹﭺﭻﭼﭽ
ﭾ
አላህም የምትደብቁትንና የምትገልጹትን ሁሉ ያውቃል፡፡
Verse 20
እነዚያም ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ምንንም አይፈጥሩም፡፡ እነርሱም ይፈጠራሉ፤
Verse 21
ሕያው ያልኾኑ ሙታን ናቸው፡፡ መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም፡፡
Verse 22
አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ልቦቻቸው ከሓዲዎች ናቸው፡፡ እነሱም የኮሩ ናቸው፤ (አያምኑም)፡፡
Verse 23
አላህ የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ሁሉ የሚያውቅ ለመኾኑ ጥርጣሬ የለበትም፡፡ እርሱ ኩሩዎችን አይወድም፡፡
Verse 24
ለእነርሱም «ጌታችሁ (በሙሐመድ ላይ) ምንን አወረደ» በተባሉ ጊዜ «(እርሱ) የመጀመሪያዎቹ ሕዝቦች ተረቶች ነው» ይላሉ፡፡
Verse 25
(ይህንንም የሚሉት) በትንሣኤ ቀን ኀጢኣቶቻቸውን በሙሉ ከእነዚያም ያለ ዕውቀት ኾነው ከሚያጠሟቸው ሰዎች ኀጢአቶች ከፊሉን ሊሸከሙ ነው፡፡ ንቁ! የሚሸከሙት ኃጢኣት ምንኛ ከፋ!
Verse 26
እነዚያ ከእነሱ (ከቁረይሾች) በፊት የነበሩት በእርግጥ መከሩ፡፡ አላህም ሕንጻዎቻቸውን ከመሠረቶቻቸው አፈረሰ፡፡ ጣሪያውም በእነሱ ላይ ከበላያቸው ወደቀባቸው፡፡ ቅጣቱም ከማያውቁት ሥፍራ መጣባቸው፡፡
Verse 27
ከዚያም በትንሣኤ ቀን ያዋርዳቸዋል፡፡ እነዚያም «በእነሱ (ጉዳይ) ትከራከሩኝ የነበራችሁት ተጋሪዎቼ የት ናቸው» ይላቸዋል፡፡ «እነዚያ ዕውቀትን የተሰጡት ዛሬ ሐፍረቱና ቅጣቱ በእርግጥ በከሓዲዎች ላይ ነው» ይላሉ፡፡
Verse 28
(እነርሱ) «እነዚያ ነፍሶቻቸውን በዳይ ኾነው መላእክት የሚገድሏቸው ናቸው፡፡ ከክፉ ሥራ ምንም ነገር የምንሠራም አልነበርን» (ሲሉ) ታዛዥነታቸውን ይገልጻሉ፡፡ «በእውነት አላህ ትሰሩት የነበራችሁትን ነገር ዐዋቂ ነው» (ይባላሉ)፡፡
Verse 29
«የገሀነምንም ደጃፎች በውስጧ ዘውታሪዎች ስትኾኑ ግቡ» (ይባላሉ)፡፡ የኩሩዎችም መኖሪያ (ገሀነም) በእርግጥ ከፋች!
Verse 30
ለእነዚያም ለተጠነቀቁት «ጌታችሁ ምንን ነገር አወረደ» ተባሉ፡፡ «መልካምን ነገር» አሉ፡፡ ለእነዚያ ደግ ለሠሩት በዚሀች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ኑሮ አላቸው፡፡ የመጨረሻይቱም አገር በእርግጥ በላጭ ናት፡፡ የጥንቁቆቹም አገር ምን ታምር!
Verse 31
(እርሷም) የሚገቡዋትና በሥርዋ ወንዞች የሚፈሱባት ስትኾን የመኖሪያ አትክልቶች ናት፡፡ ለእነሱም በወስጧ የሚሹት ሁሉ አላቸው፡፡ እንደዚሁ አላህ ጥንቁቆችን ይመነዳል፡፡
Verse 32
እነዚያ በመልካም ኹኔታ ላይ ኾነው መላእክት «ሰላም በእናንተ ላይ» እያሉ የሚገድሏቸው ናቸው፡፡ «ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ገነትን ግቡ» (ይባላሉ)፡፡
Verse 33
(ከሓዲዎች) መላእክት ወደ እነሱ መምጣትን ወይም የጌታህ ትእዛዝ መምጣቱን እንጂ አይጠባበቁም፡፡ ከእነሱ በፊት የነበሩት እንደዚህ ሠርተዋል፡፡ አላህም አልበደላቸውም፤ ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ፡፡
Verse 34
የሠሩዋቸውም ኀጢአቶች (ቅጣት) አገኛቸው፡፡ በእርሱም ይሳለቁበት የነበሩት ሁሉ በነሱ ላይ ወረደባቸው፡፡
Verse 35
እነዚያም (ጣዖታትን) ያጋሩት «አላህ በሻ ኖሮ ከእርሱ ሌላ እኛም አባቶቻችንም ምንንም ባልተገዛን ነበር፤ ያለእርሱም (ትእዛዝ) ምንንም እርም ባላደረግን ነበር አሉ፡፡» እነዚያም ከነሱ በፊት የነበሩት እነደዚሁ ሠሩ፡፡ በመልክተኞቹም ላይ ግልፅ ማድረስ ብቻ እንጂ ሌላ የለባቸውም፡፡
Verse 36
በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፡፡ ከእነሱም ውስጥ አላህ ያቀናው ሰው አልለ፡፡ ከእነሱም ውስጥ በእርሱ ላይ ጥመት የተረጋገጠበት ሰው አልለ፡፡ በምድርም ላይ ኺዱ፤ የአስተባባዮችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከቱ፡፡
Verse 37
በመቅናታቸው ላይ ብትጓጓ (ምንም ልታደርግ አትችልም)፡፡ አላህ የሚጠመውን ሰው አያቀናውምና፡፡ ለእነሱም ከረዳቶች ምንም የላቸውም፡፡
Verse 38
መሓሎቻቸውምን አላህ የሚሞትን ሰው አያስነሳም ሲሉ በአላህ ስም ማሉ፡፡ ሐሰት ነው (ያስነሳቸዋል)፡፡ በእርሱ ላይ ቃል ኪዳን ገብቷል፡፡ አረጋግጧል፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም፡፡
Verse 39
(የሚቀሰቅሳቸውም) ለእነሱ ያንን በእርሱ የሚለያዩበትን ሊገልጽላቸው፤ እነዚያ የካዱትም እነሱ ውሸታሞች የነበሩ መኾናቸውን እንዲያውቁ ነው፡፡
Verse 40
ለማንኛውም ነገር (መኾኑን) በሻነው ጊዜ ቃላችን ለእርሱ «ኹን» ማለት ብቻ ነው፤ ወዲውም ይኾናል፡፡
Verse 41
እነዚያም ከተበደሉ በኋላ በአላህ (መንገድ ላይ) የተሰደዱት በቅርቢቱ ዓለም መልካሚቱን አገር (መዲናን) በእርግጥ እናሰፍራቸዋለን፡፡ የመጨረሻይቱም ዓለም ምንዳ ታላቅ ነው፡፡ (ከሓዲዎች) ቢያውቁ ኖሮ (በተከተሏቸው ነበር)፡፡
Verse 42
ﰄﰅﰆﰇﰈ
ﰉ
(እነርሱ) እነዚያ የታገሱት በጌታቸውም ላይ የሚጠጉት ናቸው፡፡
Verse 43
ከአንተም በፊት ወደእነሱ ወሕይን (ራእይን) የምናወርድላቸውን ሰዎችን እንጂ ሌላን አልላክንም፡፡ የማታውቁም ብትኾኑ የዕውቀትን ባለቤቶች ጠይቁ፡፡
Verse 44
በግልጽ ማስረጃዎችና በመጻሕፍት (ላክናቸው)፡፡ ወደ አንተም ለሰዎች ወደእነሱ የተወረደውን (ፍች) ልትገልጽላቸውና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን፡፡
Verse 45
እነዚያ መጥፎዎችን የዶለቱ አላህ በእነሱ ምድርን የሚገለብጥባቸው ወይም ከማያውቁት ስፍራ ቅጣት የሚመጣባቸው መኾኑን አይፈሩምን
Verse 46
ወይም (ካገር ወደ አገር) በሚዛወሩበት ጊዜ የሚይዛቸው መኾኑን (አይፈሩምን) እነሱም አሸናፊዎች አይደሉም፡፡
Verse 47
ወይም ቀስ በቀስ በማጉደል ላይ የሚይዛቸው መኾኑን (አይፈሩምን) ጌታችሁም በእርግጥ ርኅሩኅ አዛኝ ነው፡፡
Verse 48
ወደዚያ ከማንኛውም ነገር አላህ ወደ ፈጠረው ጥላዎቹ እነርሱ የተዋረዱ ሲኾኑ ለአላህ ሰጋጆች ኾነው ከቀኝና ከግራዎች ወደሚዛወሩት አላዩምን
Verse 49
ለአላህም በሰማያት ያለው ከተንቀሳቃሽም በምድር ያለው ሁሉ፣ መላእክትም ይሰግዳሉ፡፡ እነርሱም አይኮሩም፡፡
Verse 50
ጌታቸውን ከበላያቸው ሲኾን ይፈሩታል፡፡ የታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ፡፡
Verse 51
አላህም አለ «ሁለት አማልክትን አትያዙ፡፡ እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እኔንም ብቻ ፍሩ፡፡»
Verse 52
በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ መገዛትም ዘወትር ሲኾን ለርሱ ብቻ ነው፡፡ ከአላህም ሌላ ያለን ትፈራላችሁን
Verse 53
ማንኛውም በእናንተ ላይ ያለው ጸጋ ከአላህ ነው፡፡ ከዚያም ችግር በደረሰባችሁ ጊዜ ወደርሱ ብቻ ትጮሃላችሁ፡፡
Verse 54
ከዚያም ከእናንተ ላይ ችግርን ባነሳላችሁ ጊዜ ከእናንተው የኾኑ ጭፍሮች ወዲያውኑ በጌታቸው (ጣዖትን) ያጋራሉ፡፡
Verse 55
(የሚያጋሩትም) በሰጠናቸው ሊክዱ ነው፡፡ ተጠቀሙም ወደ ፊትም (የሚደርስባችሁን) በእርግጥ ታውቃላችሁ፡፡
Verse 56
ለማያውቁትም (ጣዖታት) ከሰጠናቸው ሲሳይ ፈንታን ያደርጋሉ፡፡ በአላህ እምላለሁ፤ ትቀጣጥፉት ከነበራችሁት ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ፡፡
Verse 57
ለአላህም (ከመላእክት) ሴቶች ልጆችን ያደርጋሉ፡፡ ጥራት ተገባው፡፡ ለእነርሱም የሚፈልጉትን (ወንዶች ልጆችን) ያደርጋሉ፡፡
Verse 58
አንዳቸውም በሴት ልጅ በተበሰረ ጊዜ እርሱ የተቆጨ ኾኖ ፊቱ ጠቁሮ ይውላል፡፡
Verse 59
በእርሱ ከተበሰረበት ነገር መጥፎነት በውርደት ላይ ኾኖ ይያዘውን ወይስ በዐፈር ውስጥ ይደብቀውን (በማለት እያምታታ) ከሰዎች ይደበቃል፡፡ ንቁ! የሚፈርዱት (ፍርድ) ምንኛ ከፋ!
Verse 60
ለእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም ለማያምኑት መጥፎ ጠባይ አላቸው፡፡ ለአላህም ታላቅ ባሕርይ አለው፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡
Verse 61
አላህም ሰዎችን በበደላቸው በያዛቸው ኖሮ በርሷ (በምድር ላይ) ከተንቀሳቃሽ ምንንም ባልተወ ነበር፡፡ ግን እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ያቆያቸዋል፡፡ ጊዜያቸውም በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይቆዩም፤ አይቀደሙምም፡፡
Verse 62
ለአላህም የሚጠሉትን ነገር ያደረጋሉ፡፡ ለእነሱም መልካሚቱ (አገር) አለቻቸው በማለት ምላሶቸቸው ውሸትን ይናገራሉ፡፡ ለእነሱ እሳት ያለቻቸው መኾናቸውና እነሱም (ወደርሷ) በቅድሚያ የሚነዱ መኾናቸው ጥርጥር የለበትም፡፡
Verse 63
በአላህ እንምላለን፤ ካንተ በፊት ወደ ነበሩት ሕዝቦች በእርግጥ (መልክተኞችን) ልከናል፡፡ ሰይጣንም ለእነርሱ ሥራዎቻቸውን ሸለመላቸው፡፡ እርሱም ዛሬ ረዳታቸው ነው፡፡ ለእነሱም (ኋላ) አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡
Verse 64
ባንተም ላይ መጽሐፉን አላወረድንም፤ ያንን በርሱ የተለያዩበትን ለነርሱ ልታብራራላቸውና ለሚያምኑትም ሕዝቦች መሪና እዝነት ሊኾን እንጂ፡፡
Verse 65
አላህም ከሰማይ ውሃን አወረደ፡፡ በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው አደረገ፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አልለ፡፡
Verse 66
ለናንተም በግመል፣ በከብት፣ በፍየል በእርግጥ መገምገሚያ አልላችሁ፡፡ በሆዶቹ ውስጥ ካለው ከፈረስና ከደም መካከል ጥሩ ወተትን ለጠጪዎች ተዋጭ ሲሆን እናጠጣችኋለን፡፡
Verse 67
ከዘምባባዎችና ከወይኖችም ፍሬዎች (እንመግባችኋለን)፡፡ ከእርሱ ጠጅንና መልካም ምግብንም ትሠራላችሁ፡፡ በዚህም ውስጥ ለሚያስቡ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አልለ፡፡
Verse 68
ጌታህም ወደ ንብ እንዲህ ሲል አስታወቀ «ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ (ሰዎች) ከሚሠሩትም (ቀፎ) ቤቶችን ያዢ፡፡
Verse 69
«ከዚያም ከፍሬዎች ሁሉ ብይ፡፡ የጌታሽንም መንገዶች (ላንቺ) የተገሩ ሲኾኑ ግቢ፡፡» ከሆዶችዋ መልኮቹ የተለያዩ መጠጥ ይወጣል፡፡ በእርሱ ውስጥ ለሰዎች መድኃኒት አለበት፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አልለበት፡፡
Verse 70
አላህም ፈጠራችሁ፤ ከዚያም ይገድላችኋል፡፡ ከእናንተም ከዕወቅት በኋላ ምንንም ነገር እንዳያውቅ ወደ ወራዳ ዕድሜ የሚመለስ ሰው አልለ፡፡ አላህ ዐዋቂ ቻይ ነው፡፡
Verse 71
አላህም ከፊላችሁን በከፊሉ ላይ በሲሳይ አበለጠ፡፡ እነዚያም በላጭ የተደረጉት ሲሳያቸውን እጆቻቸው በያዙዋቸው (ባሮች) ላይ እነሱ በእርሱ ይተካከሉ ዘንድ መላሾች አይደሉም፡፡ ታዲያ በአላህ ጸጋ (ለእርሱ ተጋሪ በማድረግ) ይክዳሉን
Verse 72
አላህም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ለእናንተ ሚስቶችን አደረገ፡፡ ለእናንተም ከሚስቶቻችሁ ወንዶች ልጆችን፣ የልጅ ልጆችንም አደረገላችሁ፡፡ ከመልካሞችም ጸጋዎች ሰጣችሁ፡፡ ታድያ በውሸት (በጣኦት) ያምናሉን በአላህም ጸጋ እነሱ ይክዳሉን
Verse 73
ከአላህም ሌላ ከሰማያትም ከምድርም ምንንም ሲሳይ የማይሰጧቸውን (ምንንም) የማይችሉትንም ይግገዛሉ፡፡
Verse 74
ለአላህም አምሳያዎችን አታድርጉ፡፡ አላህ (መሳይ እንደሌለው) ያውቃል፡፡ እናንተ ግን አታውቁም፡፡
Verse 75
በምንም ላይ የማይችለውን በይዞታ ያለውን ባሪያና ከእኛ መልካም ሲሳይን የሰጠነውን እርሱም ከእርሱ (ከሰጠነው) በምስጢርና በግልጽ የሚለግሰውን (ነጻ) ሰው አላህ (ለጣዖትና ለርሱ) ምሳሌ አደረገ፡፡ (ሁለቱ) ይተካከላሉን ምስጋና ለአላህ ይኹን፡፡ በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡
Verse 76
አላህም ሁለትን ወንዶች (ለከሓዲና ለምእመን) ምሳሌ አደረገ፡፡ አንደኛቸው በምንም ነገር ላይ የማይችል ዲዳ ነው፡፡ እርሱም በጌታው ላይ ሸክም ነው፡፡ ወደ የትም ቢያዞረው በደግ ነገር አይመጣም፡፡ እርሱና ያ እርሱ በቀጥተናው መንገድ ላይ ኾኖ በማስተካከል የሚያዘው ሰው ይስተካከላሉን
Verse 77
በሰማያትና በምድርም ያለው ሩቅ ምስጢር የአላህ ነው፡፡ የሰዓቲቱም ነገር (መምጣቷ) እንደዓይን ቅጽበት እንጂ አይደለም፡፡ ወይ እርሱ ይበልጥ የቀረበ ነው፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡
Verse 78
አላህም ከእናቶቻችሁ ሆዶች ምንም የማታውቁ ሆናችሁ አወጣችሁ፡፡ ታመሰግኑም ዘንድ ለእናንተ መስሚያን ማያዎችንም ልቦችንም አደረገላችሁ፡፡
Verse 79
ወደ በራሪዎች በሰማይ አየር ውስጥ (ለመብረር) የተገሩ ሲኾኑ (ከመውደቅ) አላህ እንጂ ሌላ የማይዛቸው ኾነው አይመለከቱምን በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምራቶች አሉ፡፡
Verse 80
አላህም ከቤቶቻችሁ ለእናንተ መርጊያን አደረገላችሁ፡፡ ከእንስሳዎችም ቆዳዎች በጉዟችሁ ቀን በመቀመጫችሁም ቀን የምታቀልላቸውን ቤቶች ለናንተ አደረገላችሁ፡፡ ከበግዋ ሱፎች፣ ከግመልዋም ጠጉሮች፣ ከፍየልዋም ጠጉሮች የቤት ዕቃዎችን እስከ ጊዜም ድረስ መጠቃቀሚያን (አደረገላችሁ)፡፡
Verse 81
አላህም ከፈጠረው ነገር ለእናንተ ጥላዎችን አደረገላችሁ፡፡ ከጋራዎችም ለእናንተ መከለያዎችን አደረገላችሁ፡፡ ሐሩርንም (ብርድንም) የሚጠብቋችሁን ልብሶች የጦራችሁንም አደጋ የሚጠብቋችሁን ጥሩሮች ለእናንተ አደረገላችሁ፡፡ እንደዚሁ ትሰልሙ ዘንድ ጸጋውን በእናንተ ላይ ይሞላል፡፡
Verse 82
ﮆﮇﮈﮉﮊﮋ
ﮌ
(ከኢስላም) ቢሸሹም ባንተ ላይ ያለብህ ግልጽ ማድረስ ብቻ ነው፡፡
Verse 83
የአላህን ጸጋ ያውቃሉ፡፡ ከዚያም ይክዷታል፡፡ አብዛኞቻቸውም ከሓዲዎቹ ናቸው፡፡
Verse 84
ከየሕዝቡም ሁሉ መስካሪን የምንቀሰቅስበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ ከዚያም ለእነዚያ ለካዱት (ንግግር) አይፈቀድላቸውም፡፡ እነሱም በወቀሳ አይታለፉም፡፡
Verse 85
እነዚያም የበደሉት ቅጣቱን ባዩ ጊዜ ከእነሱ (ቅጣቱ) አይቀለልላቸውም፡፡ እነሱም ጊዜ አይስሰጡም፡፡
Verse 86
እነዚያም ያጋሩት የሚያጋሩዋቸውን ባዩ ጊዜ «ጌታችን ሆይ! እነዚህ ከአንተ ሌላ እንገዛቸው የነበርነው ተጋሪዎቻችን ናቸው» ይላሉ፡፡ (አማልክቶች) «እናንተ በእርግጥ ውሸታሞች ናችሁ» የማለትንም ቃል ወደእነሱ ይጥላሉ፡፡
Verse 87
(አጋሪዎቹ) በዚያ ቀንም ታዛዥነታቸውን ወደ አላህ ያቀርባሉ፡፡ ይቀጣጥፉት የነበሩትም ሁሉ ከእነርሱ ይጠፋቸዋል፡፡
Verse 88
እነዚያ የካዱ፣ ከአላህም መንገድ የከለከሉ ያጠፉ በነበሩት ምክንያት ቅጣትን በቅጣት ላይ ጨመርንባቸው፡፡
Verse 89
በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ ከጎሳቸው በእነሱ ላይ መስካሪን የምንቀሰቅስበትን አንተንም በእነዚህ (ሕዝቦች) ላይ መስካሪ አድርገን የምናመጣህን ቀን (አስታውስ)፡፡ መጽሐፉንም ለሁሉ ነገር አብራሪ፣ መሪም፣ እዝነትም፣ ለሙስሊሞችም አብሳሪ ኾኖ ባንተ ላይ አወረድነው፡፡
Verse 90
አላህ በማስተካከል፣ በማሳመርም፣ ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፡፡ ከአስከፊም (ከማመንዘር)፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ፣ ከመበደልም ይከለክላል፡፡ ትገነዘቡ ዘንድ ይገስጻችኋል፡፡
Verse 91
ቃል ኪዳንም በገባችሁ ጊዜ በአላህ ቃል ኪዳን ሙሉ፡፡ መሓሎቻችሁንም ከአጠነከራችኋት በኋላ አላህን በእናንተ ላይ በእርግጥ መስካሪ ያደረጋችሁ ስትኾኑ አታፍርሱ፡፡ አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃልና፡፡
Verse 92
(ቃል ኪዳናችሁን በማፍረስ አንዲቱ) ሕዝብ እርሷ ከ(ሌላይቱ) ሕዝብ የበዛች ለመኾንዋ በመካከላችሁ መሓሎቻችሁን (ለክዳት) መግቢያ አድርጋችሁ የምትይዙ ስትኾኑ እንደዚያች ፈትልዋን ከጠነከረ በኋላ ትርትሮች አድርጋ እንዳፈረሰችው (ሴት) አትኹኑ፡፡ አላህ በእርሱ ይሞክራችኋል፤ በትንሣኤ ቀንም በእርሱ ትለያዩበት የነበራችሁትን ነገር ለእናንተ በእርግጥ ያብራራላችኋል፡፡
Verse 93
አላህም በሻ ኖሮ አንዲት ሕዝብ ባደረጋችሁ ነበር፡፡ ግን የሚሻውን ሰው ያጠማል፡፡ የሚሻውንም ሰው ያቀናል፡፡ ትሠሩት ከነበራችሁትም ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ፡፡
Verse 94
ጫማዎች ከተደላደሉ በኋላ እንዳይንዳለጡ ከአላህም መንገድ በመከልከላችሁ ምክንያት ቅጣትን እንዳትቀምሱ መሓሎቻችሁን በመካከላችሁ ለክዳት መግቢያ አድርጋችሁ አትያዙ፡፡ ለእናንተም (ያን ጊዜ) ታላቅ ቅጣት አላችሁ፡፡
Verse 95
በአላህም ቃል ኪዳን ጥቂትን ዋጋ አትግዙ፡፡ የምታውቁ ብትኾኑ አላህ ዘንድ ያለው ምንዳ እርሱ ለእናንተ በላጭ ነውና፡፡
Verse 96
እናንተ ዘንድ ያለው ሁሉ ያልቃል፡፡ አላህ ዘንድ ያለው ግን (ዘለዓለም) ቀሪ ነው፡፡ እነዚያንም የታገሱትን ይሠሩት በነበሩት በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን፡፡
Verse 97
ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን፡፡
Verse 98
ቁርኣንንም ባነበብህ ጊዜ እርጉም ከኾነው ሰይጣን በአላህ ተጠበቅ፡፡
Verse 99
እርሱ በእነዚያ ባመኑትና በጌታቸው ላይ በሚጠጉት ላይ ለእርሱ ስልጣን የለውምና፡፡
Verse 100
ስልጣኑ በእነዚያ በሚታዘዙት ላይና በእነዚያም እነርሱ በእርሱ (ምክንያት) አጋሪዎች በኾኑት ላይ ብቻ ነው፡፡
Verse 101
በአንቀጽም ስፍራ አንቀጽን በለወጥን ጊዜ አላህም የሚያወርደውን ነገር አዋቂ ነው፡፡ «አንተ ቀጣፊ እንጂ ሌላ አይደለህም» ይላሉ፡፡ በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡
Verse 102
እነዚያን ያመኑትን ለማረጋጋት ሙስሊሞቹንም ለመምራትና ለማብሰር (ቁርኣንን) ቅዱሱ መንፈስ (ጂብሪል) እውነተኛ ሲኾን ከጌታህ አወረደው በላቸው፡፡
Verse 103
እነርሱም «እርሱን (ቁርኣንን) የሚያስተምረው ሰው ብቻ ነው» ማለታቸውን በእርግጥ እናውቃለን፡፡ የዚያ ወደርሱ የሚያስጠጉበት ሰው ቋንቋ ዐጀም ነው፡፡ ይህ (ቁርአን) ግን ግልጽ ዐረብኛ ቋንቋ ነው፡፡
Verse 104
እነዚያን በአላህ አንቀጾች የማያምኑትን አላህ አይመራቸውም፤ ለነሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡
Verse 105
ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ብቻ ናቸው፡፡ እነዚያም ውሸታሞቹ እነሱ ብቻ ናቸው፡፡
Verse 106
ከእምነቱ በኋላ በአላህ የካደ ሰው (ብርቱ ቅጣት አልለው)፡፡ ልቡ በእምነት የረጋ ኾኖ (በክህደት ቃል በመናገር) የተገደደ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡ ግን ልባቸውን በክሕደት የከፈቱ ሰዎች በነሱ ላይ ከአላህ ቁጣ አለባቸው፡፡ ለእነሱም ታላቅ ቅጣት አልላቸው፡፡
Verse 107
ይህ (ቅጣት) እነሱ ቅርቢቱን ሕይወት ከመጨረሻይቱ በመምረጣቸው ምክንያትና አላህም ከሓዲዎችን ሕዝቦች የማያቀና በመኾኑ ነው፡፡
Verse 108
እነዚያ እነርሱ በልቦቻቸው፣ በዓይኖቻቸውም፣ በጆሮዎቻቸውም ላይ አላህ ያተመባቸው ናቸው፡፡ እነዚያም ዝንጉዎቹ እነሱ ናቸው፡፤
Verse 109
እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ከሳሪዎቹ እነሱ ለመኾናቸው ጥርጥር የለም፡፡
Verse 110
ከዚያም ጌታህ ለእነዚያ ከተፈተኑ በኋላ ለተሰደዱት ከዚያም ለታገሉትና ለታገሱት (መሓሪ አዛኝ ነው)፡፡ ጌታህ ከእርሷ (ከፈተናዋ) በኋላ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
Verse 111
ነፍስ ሁሉ ከራሷ ላይ የምትከራከር ኾና የምትመጣበትን ነፍስም ሁሉ የሠራችውን (ዋጋ) የምትቀበልበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡
Verse 112
አላህ ጸጥተኛ፣ የረካች፣ ሲሳይዋ ሰፊ ኾኖ ከየስፍራው ይመጣላት የነበረችውንና በአላህ ጸጋዎች የካደችውን አላህም ይሠሩት በነበሩት ኃጢኣት የረኃብንና የፍርሃትን ቅጣቶች ያቀመሳትን ከተማ (መካን) ምሳሌ አደረገ፡፡
Verse 113
ከእነርሱ ውስጥ የኾነ መልክተኛም በእርግጥ መጣላቸው፡፡ አስተባበሉትም፡፡ እነሱም በዳዮች ኾነው ቅጣቱ ያዛቸው፡፡
Verse 114
አላህም ከሰጣችሁ ሲሳይ የተፈቀደ ንጹሕ ሲኾን ብሉ፡፡ የአላህንም ጸጋ እርሱን የምትገዙት ብትሆኑ አመስግኑ፡፡
Verse 115
በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትንና ደምን፣ የአሳማንም ስጋ፣ ያንንም (በመታረድ ጊዜ) በእርሱ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ብቻ ነው፡፡ አመጸኛም ወሰን አላፊም ሳይኾን (ለመብላት) የተገደደ ሰው (ይፈቀድለታል)፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
Verse 116
በአላህም ላይ ውሸትን ልትቀጣጥፉ ምላሶቻችሁ በሚመጥኑት ውሸት «ይህ የተፈቀደ ነው፤ ይህም እርም ነው» አትበሉ፡፡ እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ አይድኑም፡፡
Verse 117
ﯤﯥﯦﯧﯨ
ﯩ
ጥቂት መጣቀም አላቸው፡፡ ለእነሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡
Verse 118
በእነዚያም ይሁዳውያን በኾኑት ላይ ከአሁን በፊት በአንተ ላይ የተረክነውን ነገር እርም አድርገንባቸዋል፡፡ እኛም አልበደልናቸውም፡፡ ግን ነፍሶቻቸውን ይበድሉ ነበሩ፡፡
Verse 119
ከዚያም ጌታህ ለእነዚያ በስሕተት መጥፎን ለሠሩና ከዚያም ከዚህ በኋላ ለተጸጸቱ ሥራቸውንም ላበጁ ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
Verse 120
ኢብራሂም ለአላህ ታዛዥ ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ተዘንባይ ሕዝብ ነበር፡፡ ከአጋሪዎቹም አልነበረም፡፡
Verse 121
ለጸጋዎቹ አመስጋኝ ነበር፤ መረጠው፡፡ ወደ ቀጥተኛውም መንገድ መራው፡፡
Verse 122
በቅርቢቱም ዓለም በጎን ነገር ሰጠነው፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም በእርግጥ ከመልካሞቹ ነው፡፡
Verse 123
ከዚያም ወደ አንተ የኢብራሂምን ሃይማኖት ቀጥተኛ ሲኾን ተከተል፤ ከአጋሪዎቹም አልነበረም ማለት አወረድን፡፡
Verse 124
ሰንበት (ክልክል) የተደረገው በእነዚያ በእርሱ በተለያዩበት ሰዎች ላይ ብቻ ነው፡፡ ጌታህም በትንሣኤ ቀን ይለያዩበት በነበሩት ነገር በመካከላቸው በእርግጥ ይፈርዳል፡፡
Verse 125
ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡ በዚያችም እርሷ መልካም በኾነችው (ዘዴ) ተከራከራቸው፡፡ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ቅን የኾኑትን ሰዎች ዐዋቂ ነው፡፡
Verse 126
ብትበቀሉም በርሱ በተቀጣችሁበት ብጤ ተበቀሉ፡፡ ብትታገሱም እርሱ ለታጋሾች በእርግጥ በላጭ ነው፡፡
Verse 127
ታገስም፤ መታገስህም በአላህ (ማስቻል) እንጂ አይደለም፡፡ በእነርሱም ላይ (ባያምኑ) አትተክዝ፡፡ (ባንተ ላይ) ከሚመክሩትም ተንኮል በጭንቀት ውስጥ አትኹን፡፡
Verse 128
አላህ ከእነዚያ ከሚፈሩትና ከእነዚያም እነሱ መልካም ሠሪዎች ከኾኑት ጋር ነውና፡፡
تقدم القراءة