የሱራ العاديات ትርጉም በالأمهرية ከSadiq and Sani - Amharic translation
Verse 1
ﮱﯓ
ﯔ
እያለከለኩ ሩዋጮች በኾኑት (ፈረሶች) እምላለሁ፡፡
Verse 2
ﯕﯖ
ﯗ
(በሰኮናቸው) እያጋጩ እሳትን አውጪዎች በኾኑትም፤
Verse 3
ﯘﯙ
ﯚ
በማለዳ ወራሪዎች በኾኑትም፤
Verse 4
ﯛﯜﯝ
ﯞ
በእርሱ አቧራን በቀሰቀሱትም፤
Verse 5
ﯟﯠﯡ
ﯢ
በ(ጠላት) ክቢ መካከል በእርሱ (በጧት) በተጋፈጡትም እምላለሁ፡፡
Verse 6
ﭑﭒﭓﭔ
ﭕ
ሰው ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው፡፡
Verse 7
ﭖﭗﭘﭙ
ﭚ
እርሱም በዚህ ላይ መስካሪ ነው፡፡
Verse 8
ﭛﭜﭝﭞ
ﭟ
እርሱም ገንዘብን ለመውደድ በጣም ብርቱ ነው፡፡
Verse 9
(ሰው) አያውቅምን? በመቃብሮች ያሉት (ሙታን) በተቀሰቀሱ ጊዜ፤
Verse 10
ﭩﭪﭫﭬ
ﭭ
በልቦች ውስጥ ያለውም ሁሉ በተገለጸ ጊዜ (እንዴት እንደሚኾን)፡፡
Verse 11
ﭮﭯﭰﭱﭲ
ﭳ
ጌታቸው በዚያ ቀን በእነርሱ (ነገር) በእርግጥ ውስጠ አዋቂ ነው፡፡
تقدم القراءة