የሱራ التكاثر ትርጉም በالأمهرية ከSadiq and Sani - Amharic translation
Verse 1
ﮣﮤ
ﮥ
በብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘነጋችሁ፡፡
Verse 2
ﮦﮧﮨ
ﮩ
መቃብሮችን እስከ ጎበኛችሁ ድረስ፡፡
Verse 3
ﮪﮫﮬ
ﮭ
ተከልከሉ፤ ወደፊት (ውጤቱን) ታውቃላችሁ፡፡
Verse 4
ﮮﮯﮰﮱ
ﯓ
ከዚያም ተከልከሉ፤ ወደ ፊት ታውቃላችሁ፡፡
Verse 5
ﯔﯕﯖﯗﯘ
ﯙ
በእውነቱ (የሚጠብቃችሁን) እርግጠኛ ዕውቀትን ብታውቁ ኖሮ፤ (ባልዘናጋችሁ ነበር)፡፡
Verse 6
ﯚﯛ
ﯜ
ገሀነምን በእርግጥ ታያላችሁ፡፡
Verse 7
ﯝﯞﯟﯠ
ﯡ
ከዚያም እርግጠኛን ማየት ታዩዋታላችሁ፡፡
Verse 8
ﯢﯣﯤﯥﯦ
ﯧ
ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ፡፡
تقدم القراءة