ترجمة سورة الرحمن

الترجمة الأمهرية
ترجمة معاني سورة الرحمن باللغة الأمهرية من كتاب الترجمة الأمهرية .
من تأليف: محمد صادق ومحمد الثاني حبيب .

አል-ረሕማን፤
ቁርኣንን አስተማረ፡፡
ሰውን ፈጠረ፡፡
መናገርን አስተማረው፡፡
ፀሐይና ጨረቃ በተወሰነ ልክ (ይኼዳሉ)፡፡
ሐረግና ዛፍም (ለእርሱ) ይሰግዳሉ፡፡
ሰማይንም አጓናት፡፡ ትክክለኛነትንም ደነገገ፡፡
በሚዛን (ስትመዝኑ) እንዳትበድሉ፡፡
መመዘንንም በትክክል መዝኑ፡፡ ተመዛኙንም አታጉድሉ፡፡
ምድርንም ለፍጡሩ አደላደላት፡፡
በውስጧ እሸት ባለ ሺፋኖች የኾኑ ዘንባባዎችም ያሉባት ስትኾን፡፡
የገለባ ባለቤት የኾነ ቅንጣትም፡፡ ባለ መልካም መዐዛ ቅጠሎችም (ያሉባት ስትኾን)፡፡
(ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ሰውን እንደ ሸክላ ከሚቅጨለጨል ደረቅ ጭቃ ፈጠረው፡፡
ጃንንም ከእሳት ከኾነ ነበልባል ፈጠረው፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
የሁለቱ ምሥራቆች ጌታ፤ የሁለቱ ምዕራቦችም ጌታ ነው፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲኾኑ ለቀቃቸው፡፡
(እንዳይዋሐዱ) በመካከላቸው ጋራጅ አልለ፡፡ (አንዱ ባንዱ ላይ) ወሰን አያልፉም፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?›
ሉልና መርጃን ከሁለቱ ይወጣል፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
እንደ ጋራዎች ኾነው በባሕር ውስጥ የተሠሩት ተንሻለዮቹም (ታንኳዎች) የእርሱ ናቸው፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው፡፡
የልቅናና የልግሥና ባለቤት የኾነው የጌታህ ፊትም ይቀራል፡፡ (አይጠፋም)፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉት ሁሉ ይለምኑታል፡፡ በየቀኑ ሁሉ እርሱ በሥራ ላይ ነው፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?›
እናንተ ሁለት ከባዶች (ሰዎችና ጋኔኖች) ሆይ! ለእናንተ (መቆጣጠር) በእርግጥ እናስባለን፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
የጋኔንና የሰው ጭፍሮች ሆይ! ከሰማያትና ከምድር ቀበሌዎች መውጣትን ብትችሉ ውጡ፡፡ በስልጣን እንጅ አትወጡም፡፡ (ግን ስልጣን የላችሁም)
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
በሁለታችሁም ላይ ከእሳት ነበልባል፣ ጭስም ይላክባችኋል፡፡ (ሁለታችሁም) አትርረዱምም፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ሰማይም በተሰነጠቀችና እንደ ጽጌረዳ፣ እንደታረበ ቆዳ በኾነች ጊዜ፤ (ጭንቁን ምን አበረታው)፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
በዚያም ቀን ሰውም ጃንም ከኃጢኣቱ ገና አይጠየቅም፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ከሓዲዎች በምልክታቸው ይታወቃሉ፡፡ አናቶቻቸውንና ጫማዎቻቸውንም ይያዛሉ፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ፡፡
ይህቺ ያቺ አመጸኞች በእርሷ ያስተባብሉባት የነበረችው ገሀነም ናት (ይባላሉ)፡፡
በእርሷና በጣም ሞቃት በኾነ ፍል ውሃ መካከል ይመላለሳሉ፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው ሁለት ገነቶች አልሉት፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
የቀንዘሎች ባለ ቤቶች የኾኑ (ገነቶች አልሉት)፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
በሁለቱ ውስጥ የሚፈስሱ ሁለት ምንጮች አልሉ፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
በሁለቱ ውስጥ ከፍራፍሬዎች ሁሉ ሁለት ዓይነቶች (እርጥብና ደረቅ) አልሉ፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
የውስጥ ጉስጉሳቸው ከወፍራም ሐር በኾኑ ምንጣፎች ላይ የተመቻቹ ሲኾኑ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡ የሁለቱም ገነቶች ፍሬ (ለለቃሚ) ቅርብ ነው፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
በውስጣቸው ከበፊታቸው (ከባሎቻቸው በፊት) ሰውም ጃንም ያልገሰሳቸው ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች (ሴቶች) አልሉ፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ልክ ያቁትና መርጃን ይመስላሉ፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎቸ በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
የበጎ ሥራ ዋጋ በጎ እንጅ ሌላ ነውን?
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ከሁለቱ ገነቶችም ሌላ ሁለት ገነቶች አልሉ፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?›
ከልምላሜያቸው የተነሳ ወደ ጥቁረት ያዘነበሉ ናቸው፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
በውስጣቸው ሁለት የሚንፏፉ ምንጮች አልሉ፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
በውስጣቸው ፍራፍሬ፣ ዘምባባም፣ ሩማንም አልለ፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
በውስጣቸው ጠባየ መልካሞች መልክ ውቦች (ሴቶች) አልሉ፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
በድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ የዓይኖቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የኾኑ ናቸው፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ከነርሱ በፊት ሰውም ጃንም አልገሰሳቸውም፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባበላላችሁ?
በሚያረገርጉ አረንጓዴ ምንጣፎችና በሚያማምሩ ስጋጃዎች ላይ የተደላደሉ ሲኾኑ (ይቀመጣሉ)፡፡
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
የግርማና የመክበር ባለቤት የኾነው ጌታህ ስም ተባረከ፡፡
Icon