ترجمة سورة النبأ

Sadiq and Sani - Amharic translation
ترجمة معاني سورة النبأ باللغة الأمهرية من كتاب Sadiq and Sani - Amharic translation .


ከምን ነገር ይጠያየቃሉ?

ከታላቁ ዜና (ከቁርኣን ይጠያየቃሉ)፡፡

ከዚያ እነርሱ በእርሱ የተለያዩበት ከኾነው፡፡

ይከልከሉ፤ ወደፊት (የሚደርስበቸውን) በእርግጥ ያውቃሉ፡፡

ከዚያም ይከልከሉ፤ ወደፊት ያውቃሉ፡፡

ምድርን ምንጣፍ አላደረግንምን?

ጋራዎችንም ችካሎች አላደረግንምን?

ብዙ ዓይነቶችም አድርገን ፈጠርናችሁ፡፡

እንቅልፋችሁንም ዕረፍት አደረግን፡፡

ሌሊቱንም ልባስ አደረግን፡፡

ቀኑንም (ለኑሮ) መስሪያ አደረግን፡፡

ከበላያችሁም ሰባትን ብርቱዎች (ሰማያት) ገነባን፡፡

አንጸባራቂ ብርሃንንም አደረግን፡፡

ከአረገዙት ደመናዎችም ተንቧቢ ውሃን አወረድን፡፡

በእርሱ እኽልንና ቅጠላ ቅጠልን እናወጣ ዘንድ (አወረድን)፡፡

የተቆላለፉ አትክልቶችንም፡፡

የመለያው ቀን የተወሰነ ጊዜ ነው፡፡

በቀንዱ በሚነፋና የተለያዩ ጭፍሮች ኾናችሁ በምትመጡ ቀን ነው፡፡

ሰማይም በምትከፈትና (ባለ) ደጃፎችም በምትኾንበት፡፡

ጋራዎችም በሚነዱበት (እንደ) ሲሪብዱም በሚኾኑበት (ቀን) ነው፡፡

ገሀነም መጠባበቂያ (ስፍራ) ናት፡፡

ለሕግ ተላላፊዎች መመለሻ ስትኾን፡፡

በውስጧ ብዙን ዘመናት ነዋሪዎች ሲኾኑ፤

በውስጧ ቅዝቃዜንም መጠጥንም አይቀምሱም፡፡

ግን ሙቅ ውሃንና እዥን (ይቀምሳሉ)፡፡

ተስማሚን ምንዳ ይምመነዳሉ፡፡

እነርሱ ምርመራን የማይፈሩ ነበሩና፡፡

በአንቀጾቻችንም ማስተባበልን አስተባበሉና፡፡

ነገሩንም ሁሉ የተጻፈ ሲኾን አጠቃለልነው፡፡

ቅመሱም ቅጣትንም እንጅ (ሌላን) አንጨምራችሁም (ይባላሉ)፡፡

ለጥንቁቆቹ መዳኛ ስፍራ አልላቸው፡፡

አትክልቶችና ወይኖችም፡፡

እኩያዎች የኾኑ ጡተ ጉቻማዎችም፡፡

የተሞሉ ብርጭቆዎችም፡፡

በውስጧ ትርፍ ቃልንም ማስዋሸትንም አይሰሙም፡፡

ከጌታህ የኾነን ምንዳ በቂ ስጦታን (ተሰጡ)፡፡

የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ በጣም አዛኝ ከኾነው (ተመነዱ)፡፡ ከእርሱ ጋር መነጋገርን አይችሉም፡፡

መንፈሱ (ጂብሪል) መላእክቶቹም የተሰለፉ ኾነው በሚቆሙ ቀን አል-ረሕማን ለእርሱ የፈቀደለትና ትክክለኛን ቃል ያለ ሰው ቢኾን እንጅ (መነጋገርን አይችሉም)፡፡

ይህ የተረጋገጠው ቀን ነው፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መመለስን ይይዛል፡፡

እኛ ሰው ሁሉ እጆቹ ያስቀደሙትን በሚያይበትና ከሓዲውም ዋ ምኞቴ! ምንነው ዐፈር በኾንኩ በሚልበት ቀን ቅርብ የኾነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ፡፡
Icon